አራት የሞስኮ ትምህርት ቤቶች አማርኛ ቋንቋ ማስተማር ሊጀምሩ ነው
ሩሲያ ሶማልኛ፣ ዙሉ እና ዙርባ የተባሉ የአፍሪካ ቋንቋዎችንም ልጆቿን የማስተማር እቅድ አላት
ከፊታችን መስከረም ወር ጀምሮ በ4 ትምህርት ቤቶች የአማርኛና የስዋሂሊ ቋንቋ መሰጠት ይጀምራል
ሩሲያ ከፊታችን መስከረም ወር ጀምሮ አማርኛ እና ህዋህሊ ቋንቋዎችን በሞስኮ በሚገኙ በአራት ትምህርተ ቤቶች ማስተማር እንደምትጀምር አስታውቃለች።
በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ እንዳስታወቁት፤ በፈረንጆቹ ከፊታችን መስከረም 1 2023 ጀምሮ በሞስኮ በሚገኙ አራት ትምህ ቤቶች የአፍሪካ ቋንቋዎችን መስተማር ይጀመራል።
አሌክሲ ማስሎቭ ይህንን ያሉት በሩሲያ እና አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ተስፋዎች ዙሪያ በተካሄደ ውይይት ላይ እንደሆነ የሩሲያው ታስ የዜና ወኪል አስነብቧል።
ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸው፤ በሳምንት አንድ ወይም ሁለት የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ለአፍሪካ ቋንቋዎች ማስተማሪያ እንዲውሉ ይደረጋል ብለዋል።
በዚህም መሰረት ስዋህሊ እና አማርኛ ቋንቋዎች በሞስኮ ውስጥ በሚገኙ አራት ትምህር ቤቶች መሰጠት ይጀምራል ያሉ ሲሆን፤ በቀጣይም ዩርባ ቋንቋ ማስተማር ይጀመራል ሲሉም ተናግረዋል።
በመቀጥልም ሶማልኛ እና የዙሉ ቋንቋዎችን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ እንደሆነም ነው በዘገባው የተመላከተው።
ከዩክሬን ጦርነት ጋር ተያይዞ ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ሀገራት ጋር ቁርሾ ውስጥ የገባቸው ሩያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በማጠናከር ላይ ትገኛለች።