ሱዳን ከሩብ ክፍለዘመን በኋላ በአሜሪካ አምባሳደር ሾመች
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ባለፈው ታህሳስ ወር ሁለቱ ሀገራት አምባሳደር ለመቀያየር ተስማምተው ነበር ብለዋል
ሱዳን ከሩብ ክፍለዘመን በኋላ በአሜሪካ አምባሳደር መሾሟን የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
ሱዳን ከሩብ ክፍለዘመን በኋላ በአሜሪካ አምባሳደር መሾሟን የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሱዳን ከአሜሪካ ጋር የነበራትን ከሁለት አስርት አመታት በላይ የቆየውን አለመግባባት ወደ ጥሩ ግንኑነት ለመመለስ በማሰብ ከሩብ ክፍለዘመን በኋላ በአሜሪካ አምባሳደር መሾሟን አስታውቋል፡፡
የቀድሞው የሱዳን መሪ የነበሩት ኦማር ሀሳን አልበሽር በህዝብ ተቃውሞ ከአንድ አመት በፊት ከስልጣን ከወረዱ በኃላ ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ቃል ገብተዋል፡፡
የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንጋፋውን ዲፕሎማት ኑረልዲን ሳቲ በዋሽንግተን ዲሲ የሱዳን አምባሳደር እንዲሆኑ የሾመ ሲሆን፣ አሜሪካም ሹመቱን አጽድቃዋለች፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ አሜሪካ በሱዳን አምባሳደር የመሾም እቅድ እንዳላትና ጊዜው መቼ እንደሆነ ምንም ፍንጭ አልሰጡም፤ ነገርግን ባለፈው መስከረም ወር ሁለቱ ሀገራት አምባሳደር ለመቀያየር የወሰኑት ውሳኔ ታሪካዊ ነው ብለዋል፡፡
ሁለቱ ሀገራት ለሩብ ክፍለዘመን ያህል በተወካይ ዲፕሎማት ተወካይ አማካኝነት በዋሽንግተንና በካርቱም የሚገኙ ኢምባሲያቸውን ሲመሩ ቆይተዋል፡፡ ባለፈው ታህሳስ ወር የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ሁለቱ ሀገራት አምባሳደር ለመቀያየር መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡
የአሜሪካ አምባሳደር የሚታጨው በፕሬዘዳንት ትራምፕ ሲሆን ሹመቱ ደግሞ በሴኔቱ መጽደቅ አለበት፡፡
የአሜሪካ መንግስት ሱዳን እስላማዊ ታጣቂዎችን ትደግፋለች በማለት ሽብርን ከሚደግፉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ በፈረንጆቹ 1993 አካታት ነበር፤ በዚህም ሱዳን ከአለም አቀፍ የሞናተሪ ፈንድና ከአለም ባንክ ብድር ለማግኘት ተቸግራ ቆይታለች፡፡
ባለፈው አመት አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለስልጣን ሱዳንን ከዝርዝሩ ሊያስወጧት እንደሚችሉ ገልጸው ነበር፡፡ አሜሪካ በፈረንጆች አቆጣጠር በ1998 ዓ.ም በኢምባሲዋ ላይ በተቃጣው ጥቃት ሱዳንን የምትከሰው አሜሪካ አሁንም ቢሆን በወቅቱ የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦች ሱዳን ካሳ እንድትከፍል ትፈልጋለች፡፡