ኢኮኖሚ
አነስተኛ ብድር ያለባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
በአልማዝ ማዕድን የበለጸገችው ቦትስዋና ዝቅተኛ ብድር ካለባቸው የዓለማችን ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ናት
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/07/258-160301--2-1-1-2-_700x400.jpg)
የዓለም ሀገራት ያለባቸው ጠቅላላ ብድር ከ100 ትሪሊዮን ዶላር አልፏል
አነስተኛ ብድር ያለባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ዓለም አቀፉ የገንዘብ አበዳሪ ተቋም አይኤምኤፍ ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት መሰረት በዓለማችን ያሉ ሀገራት አጠቃላይ ብድር 100 ትሪሊዮን ዶላር አልፏል።
በአይኤምኤፍ የ2024 ሪፖርት መሰረት አሜሪካ 35 ትሪሊዮን ዶላር እዳ ሲኖርባት በእዳ ብዛት ቀዳሚዋ ሀገር ናት።
አፍሪካዊቷ የአልማዝ ማዕድን ሀብታሟ ሀገር ቦትስዋና ደግሞ ዝቅተኛ ብድር ካለባቸው ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ናት።
ኖርዌይ፣ ስዊድን እና ሳውዲ አረቢያ ደግሞ ዝቅተኛ ብድር ካለባቸው ሀገራት መካከል ተጠቅሰዋል።
እንዲሁም አውስትራልያ ፣ የተትረፈረፈ ዩራኒየም አላት የምትባለው ካዛኪስታን፣ ኢንዶኔዥያ እና ሜክሲኮም በአንጻራዊነት አነስተኛ ብድር ያለባቸው ሀገራት እንደሆኑ በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሰዋል።