ካሊፋ ሃፍታርም ከለቢያው ምርጫ ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል
የቀድሞ የሊቢያ መሪ መአማር ጋዳፊ ልጅ ሳኢፍ አል ኢስላም ጋዳፊ ከሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዕጩነታቸው መሰረዛቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ገለጸ።
ሳኢፍ አል ኢስላም ጋዳፊን ጨምሮ ለምርጫው ሊወዳደሩ የነበሩ 25 ሰዎች ከምርጫው ውጭ እንዲሆኑ ተወስኗል ተብሏል።
98 ሰዎች ለምርጫው በዕጩነት መቅረባቸው ተገልጾ የነበረ ቢሆንም የሙአማር ጋዳፊ ልጅ ዋነኛ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብሎ ተገምቶ ነበር ተብሏል።
የቀድሞው መሪ ልጅ ከዕጩነት የተሰረዘው በሕግ የሚያስጠቀው ጉዳይ እንዳለ በመግለጽ እንደሆነ ተገልጿል።
የምስራቅ ሊቢያ ወታደራዊ ኮማንደር ካሊፋ ሃፍታርም በጦር ወንጀል እንደሚፈለጉ መገለጹ እና የአሜሪካ ዜጋ ናቸው መባሉ ከምርጫው ውጭ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ዘጋርዲየን ዘግቧል።
በሊቢያ ፖለቲካ “ሁነኛ ሰው “ የሚባሉት ሃፍታር የአሜሪካ ዜጋ እንዳልሆኑ እና የጦር ወንጀል እንዳልፈጸሙ ተናግረዋል ተብሏል።
በፈረንጆቹ ታህሳስ 24 ቀን 2021 ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው ምርጫ በርካታ ዕጩዎች መሰረዛቸው ወደ ዴሞክራሲ ትጓዛለች ተብላ የምትጠበቀው ሊቢያን ወደሌላ ቀውስ እንዳይወስዳት ያሰጋል ተብሏል።
የሊቢያ ምርጫ ኮሚሽን 98 በመቶ የሚሆኑ እጩዎችን መመዝገቡን መግለጹ ይታወሳል።