“እግር መላስ” ተማሪዎች ገቢ ለማሰባሰብ ካደረጉት ተግባር ጀርባ ያለው ታሪክ ምንድን ነው?
በአሜሪካ ኦክላህማ ተማሪዎች ገቢ ለማሰባሰብ በምላሳቸው የሰው እግር ሲልሱ ታይተዋል
ተማሪዎች በአንድ ሳምንት ውስጥ 152 ሺህ 830. ዶላር ማሰባሰብ መቻላቸው ተነግሯል
በአሜሪካ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በበጎ አድራጎት የገቢ ማሰባሰብያ ዘመቻ ላይ የሌሎችን ሰዎችን የእግር ጣቶች ሲላሱ በሚያሳዩ ምስሎች በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ መሰራጨታቸውን ተከትሎ ቁጣን አስከትሏል።
ነገሩ የተከሰተው በአሜሪካዋ ኦክላህማ በሚገኝ ዲር ክሪክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት ሲሆን፤ ሁነቱም “የክፍል ውስጥ ትግል” በሚል መጠሪያ ነው የተካሄደው።
ሁነቱም በኦክልሃማ ከተማ ውስጥ ሊገኝ “Not Your Average Joe” ለተባለ እና አካል ጉዳት እና የአዕምሮ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ብቻ ቀጥሮ ለሚያሰራ የቡና መሸጫ ድጋፍ ገቢ ለማሰባሰብ ነው።
በትናንትናው እለት አርብ “KOKH FOX 25” የተባለ የአካቢባው መገናኛ ብዙሃን 4 ተማሪዎች መሬት ላይ ተኝተው ሌሎች ወንበር ላይ የተቀመጡ አራት አዎችን የእግር ጣት በምላሳቸው ሲልሱ የሚያሳይ የ26 ሰክን ዲቪዮ ለቋል።
ይህንን ተከትሎም ቪዲዮው በቲክቶክ ላይ በርካቶች የተቀባበሉት ሲሆን፤ ከ12.9 ሚሊየን በላይ እይታ እና ከ9 ሺህ በላይ ሪፖርቶች ተደርገውበታል ነው የተባለው።
ቪዲዮውን ተከትሎም፤ “በጣም አስገራሚ እንዲሁም ይህንን ማን ፈቀደ” የሚሉ ቁጣ የተቀላቀላባቸው ምልእክቶች በስፋት እየተሰራጩ እንደሆነም ተነግሯል።
የዲር ክሪክ ትምህርት ቤት አስተዳዳሪ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ፤ በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ የበጎ ተግባር የተሳተፉ ተማሪዎች በአንድ ሳንት ውስጥ ለቡና መሸጫ ካፌው 152 ሺህ 830.38 ዶላር መሰብሰብ መቻላቸው ተነግሯል።
የኦክላህማ ፖሊስ አዛዥ ራን ዋልተርስ በበኩላቸው ተግባሩን “በአጣም አስቀያሚ” በማለት የገለጹት ሲሆን፤ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።
የኦክላህማ ስቴት የትምህርት ቢሮም የግር ጣት የመላሱን ጉዳይ እየመረመረ መሆኑን ራን ዋልተርስ ተናግረዋል።