በአሜሪካ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ49 ሺህ በላይ ዜጎች ራሳቸውን ማጥፋታቸው ተገለጸ
አሁን ላይ ያለው ራስን የማጥፋት ወንጀል በታሪክ ከፍተኛው ነው ተብሏል
በአሜሪካ ከ10 ሰዎች ውስጥ ዘጠኙ የአዕምሮ ህመም ተጠቂዎች እንደሆኑ ተገልጿል
በአሜሪካ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ49 ሺህ በላይ ዜጎች ራሳቸውን ማጥፋታቸው ተገለጸ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀይል ሀገር የሖነችው አሜሪካ የአዕምሮ ህመም ዋነኛ የጤና ስጋት እንደሆነባት አስታውቃለች፡፡
የሀገሪቱ በሽታ መከላከያ ማዕከል ወይም ሲዲሲ ባወጣው ሪፖርት መሰረት በአሜሪካ በ2022 ብቻ ራሳቸውን ያጠፉ ዜጎች ቁጥር 49 ሺህ 449 ሆኗል፡፡
በ2021 በተመሳሳይ ራሳቸውን የገደሉ አሜሪካዊያን ዜጎች ቁጥር 48 ሺህ 183 ሲሆን ይህም በ2 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
አሜሪካ ከሻወር እና ኩሽና ውሀ ፍሳሾች ቢራ ጠመቀች
ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ራስን የማጥፋት ወንጀሎች በጦር መሳሪያ የተፈጸሙ ናቸው የሚለው ሲዲሲ ጉዳዩ ትኩረት የሚስብ እንደሆነም ኣሳስቧል፡፡
ከ10 አሜሪካዊያን መካከል ዘጠኙ የአዕምሮ ህመም ተጠቂ ናቸው የተባለ ሲሆን ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው የሚያምኑት ጥቂት መሆናቸው ደግሞ ችግሩን እያባባሰው እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ይህም አሜሪካ በታሪክ ራሳቸውን ያጠፉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል የተባለ ሲሆን የሕክምና ድጋፍ መጠየቅ አሁንም ድክመት የሚመስላቸው ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡
ከ100 ሺህ አሜሪካዊያን መካከል 15 በመቶዎቹ ራሳቸውን ያጠፋሉ የተባለ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ5 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት በኒዮርክ ታዋቂ የካንሰር ሀኪም የአራት አመት ከመንፈቅ ልጇን እና ራሷን ተኩሳ ገድላለች መባሉ ይታወሳል፡፡