በቲክ ቶክ ላይ እግድ የጣሉ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
አሜሪካ ቲክ ቶክ መረጃ አሳልፎ በመስጠት የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ደቅኖብኛል የሚል ክስ ማቅረቧ ይታወሳል።
በሳይበር ሴኩሪቲ ስጋት ምክንያት በርካታ ሀገራት የመንግስት ሰራተኞች ይህን መተግበሪያ እንዳይጠቀሙ አድርገዋል
በቲክ ቶክ ላይ እግድ የጣሉ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
በርካታ ሀገራት ተወዳጅ የሆነው የቻይናው የአጫጭር ቪዲዮ መተግበሪያ ቲክ ቶክ እንዳይሰራ እግድ ጥለዋል።
በሳይበር ሴኩሪቲ ስጋት ምክንያት በርካታ ሀገራት የመንግስት ሰራተኞች ይህን መተግበሪያ እንዳይጠቀሙ አድርገዋል።
ጥቂት ሀገራት ደግሞ የቲክ ቶክ መግበሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዳይሰራ እግድ ጥለውበታል።
በተለይ አሜሪካ ቲክ ቶክ መረጃ አሳልፎ በመስጠት የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ደቅኖብኛል የሚል ክስ ማቅረቧ ይታወሳል።
ነገርግን ቲክ ቶክ መረጃ ለቻይና መንግስት አሳልፎ እንደማይሰጥ በደጋጋሚ ገልጿል።
የአሜሪካን ተጠቃሚዎችን መረጃ በአሜሪካ በማከማቸት የቻይና መንግስት እንዳይደርስበት እንደሚያደርግ እቅድ መያዙን አስታውቆ ነበር።
ይሁን እንጂ ይህ አሜሪካን አላሳመናትም።
አሜሪካ ቲክ ቶክ እንዲሸጥ ትፈልጋለች።
ብዙ መንግስታት ቲክ ቶክ እና የቻይና መንግስት ያላቸው ግንኙነት ያሳስባቸዋል።
ኤፒ ቲክ ቶክን በከፊል ወይም ሙሉ በመሉ ያገዱ ሀገራት እንደሚከተለው ዘርዝሯቸዋል።
-አፍጋኒስታን
-አውስትራሊያ
-ቤልጄየም
-ካናዳ
-ዴንማርክ
-ፈረንሳይ
-ህንድ
-ላቲቪያ
-ኔዘርላንድስ
-ኒውዝላንድ
-ፖኪስታን
-ኖርዌይ
-ታይዋን
-ዩናይትድ ኪንግደም
-አሜሪካ