ዶክተሮች የተለያዩ የካንሰር አይነቶች እንዲከሰቱ ያደርጋሉ ያሏቸውን ተገቢ ያልሆኑ የአመጋገብ ስርአቶችን እና ልሞዶችን ይፋ አድርገዋል
ካንሰርን ለመዋጋት የሚጠቅሙ ምግቦች ምን ምን ናቸው?
ዶክተሮች የተለያዩ የካንሰር አይነቶች እንዲከሰቱ ያደርጋሉ ያሏቸውን ተገቢ ያልሆኑ የአመጋገብ ስርአቶችን እና ልሞዶችን ይፋ አድርገዋል።
ዶክተር አላ ጎቢና የተባሉት የሩሲያ ጋስትሮኢንትሮሎጂስት የተመጣጠነ ምግብ በሰውነት ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንደሚያሳድር ተናግረዋል።
ዶክተር ጎቢና እንዳሉት የካንሰር ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስፈላጊ የሆኑ ማዕድናትን የያዘ ምግብ መመገብ ያስፈልጋል።
የሩሲያው ኖቮስቲ ኤጀንሲ ዶክተሩን ጠቅሶ እንደዘገበው የቱሞር እድገት ተጋላጭነትን ከ10-20 በመቶ የሚቀንሱ ምግቦች አሉ።
ፍራፍሬዎች፣አትክልቶች፣ሌጊውምስ፣ አሳ፣እንቁላል እና ቶፉ ዶክተሩ የካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳሉ ብለው የዘረዘሯቸው ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም ለውዝ እና አብዛኛው ጥራጥሬዎች፣ ወተት፣ እርጎ እና አይብም ጠቃሚ መሆናቸውን ዶክተሩ ተናግረዋል።
ዶክተር ጎቢና የተመጣጠነ ምግብ መውሰድ የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም ይጨምራል ብለዋል።
'ተራስ ፋት' እና በከፊል 'ሀይድሮጅኔትድ የሆነ ዘይት' የማሊጋንት ቱሞር ካንስር ተጋላጭነት ሊያስከትል እንደሚችል ዶክተሯ ገልጸዋል።