ሎንሊ ፕላኔት በፈረንጆቹ 2022 ዓመት ቢጎበኙ ያላቸውን የ10 ሀገራትን ዝርዝር አወጣ
ከ10ሩ ሀገራት መካከል ሶስቱ የአፍሪካ አገራት ናቸው
ተቋሙ በ2022 የሚጎበኙ ምርጥ ከተሞችን ዝርዝርንም ይፋ አድርጓል
ሎንሊ ፕላኔት በፈረንጆቹ 2022 ዓመት ቢጎበኙ በሚል የ10 ሀገራትን ዝርዝር ማውጣቱን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
ሎንሊ ፕላኔት ዋና መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው እና በየአመቱ ለጎብኚዎች መረጃ በመስጠት ይታወቃል፡፡
ይህ ተቋም መረጃ ከሁለት ወራት በኋላ በሚጀመረው በፈረንጆቹ 2022 አመት ምርጥ የጎብኚዎች መዳረሻ ይሆናሉ ያላቸውን ሀገራት ዘርዝሯል፡፡
በዚህም መሰረት በፈረንጆቹ 2022 አመት ምርጥ የጎብኚዎች መዳረሻ ይሆናሉ ካላቸው 10 ሀገራት መካከል ሶስቱ የአፍሪካ ሀገራት ሲሆኑ ሁለቱ ቀሪዎቹ የአውሮፓ እስያ እና ሰሜን አሜሪካ የገኛሉ፡፡
በአዲሱ የፈረንጆች 2022 ዓመት በአንደኝነት ይጎበኛል የተባለቸው አገር ኒውዝላንድ ቀዳሚ ሰትሆን ኖርዌይ፤ሞሪሺየስ፤በሰሜን አሜሪካ የሚገኙት እና የቀድሞዎቹ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት የነበሩት ቤሊዝ እና አንጉሊያ ደሴቶች ፤ስሎቬኒያ፤ ኦማን ፤ኔፓል፤ማለዊ እና ግብጽ በዚህ ተቋም ቢጎበኙ በሚል ለጎብኚዎች የተመረጡ አገራት ናቸው፡፡
በዚሁ ዓመት ለጎብኚዎች የተመረጡ ከተሞች ደግሞ የኒውዝላንዷ ኦክላንድ፤የቻይናዋ (ታይዋን) ታይፔ፤የጀረመኗ ፍራይበርግ፤የአሜሪካዋ አትላንታ፤የናይጀሪያዋ ሌጎስ፤የሲፕረሷ ኒኮሲያ፤ የኤየርላንዷ ደብሊን፤የሜክሲኮዋ መሪዳ፤የጣልያኗ ፍሎረንስ እና የደቡብ ኮሪያዋ ጊዮንጁ ከተሞች ለጎብኚዎች የተመረጡ ከተሞች ናቸወ፡፡