አሜሪካ ለዩክሬን በምትሰጠው ወታደራዊ እርዳታ ውስጥ የረጅም ርቀት ሮኬቶች ተካተቱ
አዲሱ ሮኬት ዩክሬን ማጥቃት የምትችልበትን ርቀት በእጥፍ የሚያሳድግ ነው ተብሏል
መሳሪያው 151 ኪ.ሜ በጓዝ ሩሲያ የተለያዩ አቅርቦት የምታመላልስበትን ምስራቃዊ ክፍል ኢላማ ውስጥ የሚያስገባ ነው ተብሏል
ዩክሬን ማጥቃት የምትችልበትን ርቀት በእጥፍ የሚያሳድግ ነው የተባለው አዲሱ ሮኬት አሜሪካ ለዩክሬን በምትሰጠው የ2 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ባለው ወታደራዊ ድጋፍ ውስጥ መካተቱን የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
አዲሱ መሳሪያ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ጦርነት አሁን ካላት መሳሪያ በእጥፍ መጓዝ የሚችል መሆኑን ሮይርስ ዘግቧል፡፡
ይህ መሳሪያ ከመሬት የሚተኮስ ቦንብ ሲሆን አሁን ባሏት ሮኬቶች የማይደረሱ ኢላማዎችን ለመምታት ያስችላታል ተብሏል፡፡
መሳሪያው 151 ኪ.ሜ በጓዝ ሩሲያ የተለያዩ አቅርቦት የምታመላልስበትን ምስራቃዊ ክፍል እና በፈረንጆቹ 2014 ሩሲያ ወደ ግዟቷ ያጠቃለለቻትን ክሪሚያን ኢላማ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡
የአሜሪካው መከላከያ እንደገለጸው ከመሬት የሚተኮስ ስሞል ዲያሜትር ቦምብ (ጂኤልኤስዲቢ) ለዩክሬን በሚሰጠው የ2 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ውስጥ ተኳቷል፡፡
ይህ ሮኬት በዩክሬን ሲደርስ አሜሪካ በፈረንጆቹ ሰኔ 2022 ካስተካከለችላት ሂምራስ ወዲህ ረጅም ርቀት ኢላማ የሚያደርግ ሮኬት ስታገኝ የመጀመሪያ ነው፡፡
77 ኪ.ሜ መጓዝ የሚችለው የሂምራስ ሮኬት ዩክሬን በፈረንጆቹ የካቲት 2022 የወረረቻትን ሩሲያ መልሶ ለማጥቃት ጥቅም ላይ ውሎ ነበር፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከከፈተች በኋላ አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን በሩሲያ ላይ በርካታ ማእቀብ ከመጣል እስከ ለዩክሬን ዘመናዊ መሳሪያ በማስታጠቅ እየተሳተፉ ነው፡፡