ሩሲያ የጠፈር ተመራማሪዎቿን ወደ መሬት ለመመለስ ሮኬት ልታመጥ ነው
ሶዩዝ የተሰኘችው ሮኬት ከአለም አቀፉ የስፔስ ጣቢያ ሶስት ተመራማሪዎችን ይዛ ትመለሳለች
ሞስኮ ባለፈው ወር የአለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ ተሳትፎዋን የሚያውክ አደጋ ገጥሟታል
ሩሲያ የጠፈር ተመራማሪዎቿን ወደ መሬት ለመመለስ ሮኬት ልታመጥ መሆኑን አስታወቀች።
የካቲት 20 2023 ላይ ያለሰው ወደ አለም አቀፉ የስፔስ ጣቢያ የምታመራው ሶይዝ ሮኬት ሶስት ተመራማሪዎችን ይዛ ወደ መሬት ትመለሳለች ተብሏል።
ሰርጌ ፕሮኮፕየቭ፣ ዲሚትሪ ፔትሊን እና ፍራንሲስኮ ሩቢዮ ናቸው ወደ መሬት ይመለሳሉ የተባለው።
እነዚህ የጠፈር ተመራማሪዎች የምትመልሰው ሮኬት ሶይዝ ኤም ኤስ 23 የሚል ስያሜ ተሰጥቷታል።
ከዚህ ቀደም ተመራማሪዎቹን ይዛ የመጠቀችው ሶዩዝ ኤም ኤስ 22 ሮኬት ባለፈው ወር የማቀዝቀዣ ክፍሏ በስብርባሪ ከዋክብት መመታቱን ሬውተርስ በዘገባው አስታውሷል።
ይህም የሩስያን የአለም አቀፍ የጠፈር ጣቢያ ( አይ ኤስ ኤስ) ተሳትፎ ማወኩ ተነግሯል።
የጠፈርተኞች የአሰሳ እንቅስቃሴ 1 ሚሊሜትር ጥልቀት ስፋት ያለውን ሽንቁር ሳይፈጥር እንዳልቀረም ጥርጣሬውን አጉልቶታል።
የተፈጠረው ችግር የናሳ ስራ ላይም ችግር መፍጠሩ ሩስያ አዲስ ሮኬት በመላክ ማስተካከያ እርምጃን ለመውሰድ ያሰበችው።
አሜሪካ ባለፈው ወርም ሞስኮ ሶዩዝ ሮኬት አምጥቃ የተወሰኑ የጠፈር ጣቢያውን አባላት ወደ መሬት መመለስ ካልቻለች አማራጮችን እንደምትልግ መግለጿ የሚታወስ ነው።