በእንግሊዝ የተዘረፉት ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን መንግስት አስታወቀ
እንግሊዞች በ1860ዎቹ በተካሄደው የመቅደላ ጦርነት ወቅት በርካታ ቅርሶችን ዘርፈው ይዘው ሄደው ነበር
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው "ሁለት በብር የተለበጡ ዋንጫዎች፣ አንድ የቀንድ ዋንጫ፣ ደብዳቤዎች እንዲሁም አንድ ጋሻ" ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል
በእንግሊዝ የተዘረፉ ቅርሶች አምስት ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን መንግስት አስታወቀ።
የአጼ ቴዎድሮስ ልጁ የልዑል አለማየሁ ፀጉርን ጨምሮ ከመቅደላ የተዘረፉ ቅርሶችን ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
እንግሊዞች በመቅደላ ጦርነት ወቅት ላጭተው የወሰዱትን የአጼ ቴዎድሮስን ጸጉር ለኢትዮጵያ መመለሳቸው ይታወሳል።
እንግሊዞች በ1860ዎቹ በተካሄደው የመቅደላ ጦርነት ወቅት በርካታ ቅርሶችን ዘርፈው ይዘው ሄደው ነበር።
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው "ሁለት በብር የተለበጡ ዋንጫዎች፣ አንድ የቀንድ ዋንጫ፣ ደብዳቤዎች እንዲሁም አንድ ጋሻ" ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ቅርስቹን ይዘው በመምጣት ለኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ማስረከባቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ሚኒስቴሩ ቅርሶቹ ለኢትዮጵያ እንዲመለሱ የወሰነው ባለፈው መስከረም ወር ነበር ብሏል።
መንግስት ከኢትዮጵያ ተዘርፈው የሄዱ እና በተለያዩ ሀገራት ሙዚየሞች የሚገኙ ቅርሶችን ለማስመለስ ጥረቱን እንደሚቀጥል ገልጿል።
እንግሊዞች ከሁለት አመት በፊት በመቅላ ጦርነት ወቅት እንግዚዞች ከኢትዮጵያ ዘርፈው የወሰዷቸው በእጅ የተጻፈ መጸሃፍ ቅዱስ፣ መስቀል፤ጦርና መጠጫዎች ጨምሮ ሌሎች ቅርሶችን መልሰው ነበር።
ቅርሶቹ በእንግሊዙ የግል አንቀሳቃሽ በሆነው ስቼሄራዛድ ፋውንዴሽን አማካኝነተ ተቀምጠው ነበር፡፡