ከመቅደላ ተዘርፈው የነበሩ ቅርሳ ቅርሶች ለኢትዮጵያ ተመለሱ
ኢምባሲው የተቀባላቸው ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱበትን መንገድ አመቻቻለሁ ብሏል
እንግሊዞች በመቅደላ ጦርነት ወቅት ላጭተው የወሰዱትን የአጼ ቴዎድሮስን ጸጉር ለኢትዮጵያ መመለሳቸው ይታወሳል
አጼ ቴዎድሮስ በፈረንጆቹ በ1868 ከእንግሊዞች ጋር በመቅደላ ባደረጉት ጦርነት ወቅት፤እንግሊዞች ዘርፈው ወስደዋቸው የነበሩት ቅርሳቅርሶች መመለሳቸውን በለንደን የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል፡፡
በመቅላ ጦርነት ወቀት እንግዚዞች ከኢትዮጵያ ዘርፈው የወሰዷቸው በእጅ የተጻፈ መጸሃፍ ቅዱስ፣ መስቀል፤ጦርና መጠጫዎች ጨምሮ ሌሎች ቅርሶች በግል አንቀሳቃሽ በሆነው ስቼሄራዛድ ፋውንዴሽን አማካኝነት ተቀምጠው ነበር፡፡
ቅርሶቹ ለኢትዮጵያ ተላልፈው በተሰጡበት ወቅት፤በሎንደን የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ፋውንዴሽኑ እነዚህን ውድ ቅርሶች ጠብቆ በማስረከቡ ያመሰገኑ ሲሆን ሎሎች የቅርስ ሰብሳቢዎችና ሙዚየሞች የመቅደላ ቅርሶችን እንዲመልሱ በድጋሚ ጠይቀዋል፡፡
የስቼሄራዛድ ፋውንዴሽን መስራች የሆኑት ጣሂር ሻህ በበኩላቸው ቅርሶቹን መመለስ ለኢትዮጵያውያን ምን ማለት አንደሆነ እናውቃልን፤ፋውንዴሽናቸው በሁለቱ ሀገራት የግንኙነት ድልድይ የመገንባት ተስፋ እንዳላቸው መግለጻቸውን ኢምባሲው ገልጿል፡፡
ኢምባሲው የተቀባላቸው ቅረሶች ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱበትን መንገድ እያመቻቸው መሆኑን ገልጿል፡፡
በመቅደላ ጦርነት ወቅት እንግሊዞች የአጼ ቴዎድሮስን ጸጉር ላጭተው ወስደው የነበረ ሲሆን ከነበረበት ሙዚየም ወደ ኢትዮጵያ መመሉ ይታወሳል፡፡