10ኛ ቀኑን ባስቆጠረው የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ዙሪያ ምን አዲስ ነገር አለ?
በሎስ አንጀስ በተቀሰቀሰው የሰደድ እሳት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 25 ደርሷል
በአሁኑ ወቅት በ6 ቦታዎች እየነደደ ያለውን እሳት ለማጥትፋት ጥረት እየተደረገ ነው
በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት 10ኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን፤ እሳቱን ለማጥፋት የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው።
በሎስ አንጀስ በተቀሰቀሰው የሰደድ እሳት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 25 ደርሷል የተባለ ሲሆን፤ ከ12 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች እና ህንጻዎች በእሳት አደጋው ወድመዋል።
በአሁኑ ወቅት እሳቱ ምን ላይ ይገኛል?
በአሁኑ ወቅት በ6 ቦታዎች እየነደደ ያለውን እሳት ለማጥትፋት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል። እሳቶቹ የሚገኘበት ስፍራም፤
የፓሊሳድስ እሳት፤ ከሶስት ዋና ዋና የሰደድ እሳቶች ትልቁ ሲሆን፤ 9 ሺህ 596 ሄክታር አቃጥሏል፤ አሁን ላይ 21 በመቶውን መቆጣጠርም ተችሏል። የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱ የጌቲ ሴንተር ሙዚየም መኖሪያ ወደሆነው ወደ ብሬንትዉድ እንዳይዛመት የመከላከል ስራ እየሰሩ ነው።
ኢቶን እሳት፡ ከሎስ አንጀለስ በሰተምስራቅ የሚገኝ፤ ይህ ሰደድ እሳት ከሞት አንፃር እጅግ አጥፊው ሲሆን፤ በኢቶን እሳት 16 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። እሳቱ 5 ሺህ 712 ሄክታር መሬት አቃጥሏል፤ አሁን ላይ 45 በመቶውን መቆጣጠርም ተችሏል።
ሀረስት እሳት፤ በሰሜን ሳን ፈርናንዶ አቅራቢያ የተቀሰቀሰው ይህ እሳት 323 ሄክታር መሬት አቃጥሏል። የእሳት አደጋ ተከላካይ ሰራተኞች አሁን ላይ 98 በመቶውን ተቆጣጥረዋል፤ ሙሉ ለሙሉ በቅጥጥር ስር ለማድረግ ተቃርበዋል.
አውቶ እሳት፤ በቬንቱራ ካውንቲ ውስጥ የተቀሰቀሰው እሳት በፍጥነት 24 ሄክታርመሬት አካሏል። የእሳት አደጋ ተከላካዮች የእሳቱን መዛመት አቁመው ነበር፣ እስከ ማክሰኞ ምሽት ድረስ የእሳቱን 85 በመቶው በቁጥጥር ስር አውለዋል።
ሊትል ማውንቴን እሳት፤ በሎስ አንጀለስ ምስራቃዊ ክፍል የሚገኘው እሳቱ አዲስ የተቀሰቀሰ ሲሆን በፍጥነት 12 ሄክታር መሬት አቃጥሏል። በበርካታ ህንጻዎች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ስጋት የደቀነው እሳቱ አሁንም በቁጥጥር ስር አልዋለም።