በኬንያ ምርጫ የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ በዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ላይ እንደማይገኙ ገለጹ
ኦዲንጋ በምርጫ ሂደቱና ውጤቱ ላይ አሁንም ድረስ “ቅሬታ አለኝ” ብለዋል
ራይላ ኦዲንጋ በበዓለ ሲመቱ ላይ የማልገኘው “ከሀገር ውጭ ስለሆንኩ ነው” ብለዋል
በኬንያ ምርጫ የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ ዛሬ በሚካሄደው “ የዶ/ር ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ላይ አልገኝም” አሉ፡፡
በዓለ ሲመት ላይ እንድገኝ ሩቶ በደብዳቤም ሆነ በስልክ ጋብዞኛል ያሉት ራይላ ኦዲንጋ፤ በተለያዩ ምክንያቶች በበዓለ ሲመቱ ላይ እንደማይገኙ አስታውቀዋል፡፡
“ባንስማማበትም የፍርድ ቤቱን ብይን እናከብራለን”- ራይላ ኦዲንጋ
ራይላ ኦዲንጋ “ከሀገር ውጭ በመሆኔ እንዲሁም አሁን ድረስ የማላምንባቸው ጉዳዮች በኖራቸው በበዓለ ሲመቱ አልገኝም”ም ብለዋል፡፡
ኦዲንጋ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነሃሴ 9 ቀን 2022 ከተደረገው ምርጫ ጋር በተያያዘ ሊወጡት የሚገባ ኃላፊነት አልተወጡም ሲሉም ያላቸው ቅሬታ ገልጸዋል፡፡
ምርጫ የማካሄድ ስልጣን የተሰጠው የኬንያ ምርጫና ድንበር ኮሚሽን “ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ አካሂዷል” ብለው እንደማያምኑም ተናግረዋል ፡፡
ኦዲንጋ፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ብይንም ቢሆን “ብንቀበለውም በመረጃና በህግ ላይ የተመሰረተ አይደለም” ብየ አምናለሁም ብለዋል ፡፡
ያም ሆኖ ወደ ሀገሬ ስመለስ ከአዚሚዮ ላ ኡሞጆ አንድ የኬንያ ቅንጅት ፓርቲ መሪዎች ጋር በመሆን ዲሞክራሲያችንን ይበልጥ ለማጠናከርና የሚያስችሉን ቀጣዩን እርምጃዎቻችን የምናሳውቅ ይሆናል ብለዋል።
ይህን ማድረግ የምንችለው “ዴሞክራሲያችንን የመጠበቅና የማሳደግ ኃላፊነት የተሰጣቸውን ቁልፍ ተቋማት ሪፎርም አድርገን ስንቀይር ብቻ ነው” ሲለም ተናግረዋል ራይላ ኦዲንጋ ።
ኦዲንጋ፤ ነሃሴ 9 ቀን 2022 ድምጽ ሊሰጧቸው ደጋፊዎቻቸውና እና ኬንያውያን ያላቸው ምስጋና ገልጸዋል፡፡