የጨረቃ ግርዶሹ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን አካባቢዎች አጋጥሟል
ዛሬ ሰኞ ንጋት አካባቢ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሙሉና ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ አጋጥሟል፡፡
የጨረቃ ግርዶሹ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያጋጠመ ነው፡፡
በአፋር ሰመራ ጨረቃ በከፊል ተጋርዳ ከንጋቱ 11፡00 አካባቢ ታይታለች፡፡
ትዕጥንቱን ብዙዎች በዐይናቸው በቴሌስኮፕ ቴክኖሎጂ ታግዘውም ለመመልከት ችለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ከሠመራ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ትዕይንቱን ሲከታተልና የዩኒቨርስቲው ተማሪዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ ትዕይንቱን የሚከታተልበትን ሁኔታ ሲያመቻች እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይህን ተፈጥሯዊ ክስተት ብዙዎች ለመከታል ፎቶ ግራፈሮችም ሁኔታውን በካሜራቸው ለማስቀረት ጥረት ሲያደርጉ ተስተውለዋል፡፡
የጨረቃ ግርዶሽ መሬት በጸሃይና ጨረቃ መካከል ስትሆን የሚከሰት ነው፡፡ በተለይ መሬት ሙሉ በሙሉ የምትሸፍን ከሆነ ጨረቃ ደም መሰል ቀለምን ትለብሳለች፡፡ ግርዶሹ የተለያዩ ደረጃዎችም ያሉት ነው፡፡
ግርዶሹ በተለያዩ የዓለማችን አካባቢዎች የተከሰተ ነው፡፡ የደቡብ አሜሪካዋ ብራዚል ዋና ከተማ ሪዮ ዲጄይኔሮ ሙሉ በሙሉ ተሸፍና ደም ለብሳ ተስተውላለች፡፡
ግርዶሹ ሙሉ በሙሉ ከመታየቱ በፊት በኒውዮርክ ማንሃታን ጨረቃ ይሄን መሳይ መልክ ነበራት፡፡
ጨረቃ ዛሬ ማለዳ ተጋርዳ ከመታየቷ በፊት የነበራት ሙሉ ቅርጽም ብዙዎችን ያስደሰተ ተፈጥሯዊ ትዕንትም ነበረ፡፡ ትናንት የነበረችው የሙሉ ጨረቃ ሁኔታም ኒውዮርክ በሚገኘው ከዓለም የንግድ ማዕከል በኩል እንዲህ ባማረ ሁኔታ ይታይ ነበረ፡፡
በጸሃይ ብርሃን መጋረድ ምክንያት አቅላልታ የተስተዋለችው ጨረቃ በከፊል ተጋርዳ ስትወጣም በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ሳን ፍራንሲስኮ ተከታዩ መልክ ነበራት፡፡
ጨረቃ ግርዶሹ በግሪክ አቴንስም ተስተውሏል፡፡ በጥንታዊው ቤተ ጣዖት ፖሴዶን የተገኙ ብዙዎች ሁነቱን እንዲህ ተከታትለዋል፡፡
በሩሲያ ሬድ ስኩዌር አደባባይም ብዙዎች ትዕንቱን ሲመለከቱ ነበረ፡፡
ጨረቃ ግንቦት ላይ እንዲህ ሆና ስትወጣ አበባዋ ጨረቃ የሚል ምላሽ ይሰጣታል፡፡ በሰሜናዊ መቄዶንያ ዋና ከተማ ስኮፔም ተከታዩ መልክ ነበራት፡፡