የሳምባ ካንሰር ክትባት በሙከራ ደረጃ መስጠት ተጀመረ
የሳምባ ካንሰር በዓለም በየ ዓመቱ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ሰዎችን ይገድላል
ተስፋ የተጣለበት አዲሱ የሙከራ ክትባት በሰባት ሃገራት በበጎ ፈቃደኞች ላይ መሰጠት ተጀምሯል
የሳምባ ካንሰር ክትባት በሙከራ ደረጃ መስጠት ተጀመረ።
በዓለማችን በገዳይነቱ የሚታወቀው የሳምባ ካንሰር እስካሁን ፈዋሽ መድሀኒት ሳይገኝለት ቆይቷል።
ተመራማሪዎች ለዓመታት ለዚህ ገዳይ ቫይረስ ፈዋሽ መድሀኒት ለመስራት ሲጥሩ የቆዩ ሲሆን ቢኤንቲ116 የሚል ስያሜ የተሰጠውን ክትባት ወደ ማምረት ተሸጋግረዋል።
ይህ ክትባት የሳምባ ካንሰርን ለመፈወስ የተዘጋጀ ሲሆን የመጨረሻ ደረጃ ከመድረሱ በፊት በሳምባ ካንሰር በተጠቁ በጎ ፈቃደኞች ላይ እየተሞከረ መሆኑን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ ይህ ክትባት በሰባት ሀገራት በሚገኙ በ38 የጥናት ማዕከላት ውስጥ ውስጥ እየተሞከረ ይገኛል።
እንግሊዝ፣ ቱርክ፣ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ስፔን እና ሌሎችም ሀገራት ክትባቱ በሙከራ ደረጃ እየተሰጠባቸው ያሉ ሀገራት ናቸው።
የሳምባ ካንሰር በዓለማችን በየ ዓመቱ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዜጎችን የሚገድል ሲሆን የሳምባ ካንሰር ከሌሎች የካንሰር አይነቶች ጋር ሲነጻጸር ተጠቂዎችን የመግደል አቅሙ ከፍተኛ እንደሆነም የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።
በሙከራ ደረጃ ያለው ይህ የሳምባ ካንሰር ክትባት የበርካቶችን ህይወት እንደሚታደግ ተስፋ ተጥሎበታል።
ሲጋራ ማጨስ፣ የተበከለ አየር፣ ለኬሚካሎች መጋለጥ፣ ለረጅም ጊዜ በቲቢ በሽታ መቆየት እና ሌሎችም ምክንያቶች ለሳምባ ካንሰር ከሚያጋልጡ ምክንያቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው።