ፖላንድ ከሉታንያ በመቀጠል በ16.9 ኪሎ ግራም የነፍስወከፍ ፍጆታ ሁለተኛ ደረጃ ይዛለች
አውሮፖዊቷ ሉታንያ በነፍስወከፍ በአይስክሬም ፍጆታ ከአለም ቀዳሚ ሀገር ሆናለች።
ሉታንያ በአይስክሬም ፍጆታ ቀደሚ የሆነችው በዘንድሮዎ አመት በተካሄደ ጥናት መሆኑ መሆኑ ተገልጿል።
ሉታንያ በፍጆታ ቁጥር አንድ የሆነችው በርካታ የአውሮፖ ሀገራትን እና አሜሪካን በመብለጥ ኘው። ፍጆታዋም 20.8 ኪሎግራም አይስክሬም ነው።
ከሉታንያ በመቀጠል ፖላንድ በ16.9 ኪሎ ግራም የነፍስወከፍ የአይስክሬም ፍጆታ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ኢስቶኒያ በ13.1 ኪ.ግ ፣ጃፖን በ12.8 ኪ.ግ፣ ማሌዥያ በ12.5ኪ.ግ ቼክ በ12.1ኪ.፣ አ ሜሪካ በ11.6 ኪ.ግ ስዊድን በ10.8 ኪ.ግ እንደቅደም ተከተላቸው ቀጣዩን ደረጃ ይዘዛል።
የዓለም አማካኝ የአይስክሬም የነፍስወከፍ ፍጆታ ፍጆታ 3.6 ኪ.ግ ነው።