የኤም23 አማጺያን ወደ ስትራቴጂካዊቷ የቡካቩ ከተማ መግባታቸው ተገለጸ
አማጺ ቡድኑ ባለፈው ጥር ወር መጨረሻ የጎማ ከተማን ከያዘ ወዲህ ወደ ደቡብ ኪቩ ግዛት ሲገሰግስ ቆይቷል።
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/16/243-121501-images-6-_700x400.jpeg)
ደሞክራሲያዊ ረፐብሊክ ኮንጎ ጎረቤቷን ሩዋንዳን የኤም23 አማጺያንን በማስታጠቅና በመርዳት ክስ እያቀረበች ነው
የኤም23 አማጺያን ወደ ስትራቴጂካዊቷን የቡካቩ ከተማ መግባታቸው ተገለጸ።
በጎረቤት ሩዋንዳ ይደገፋሉ የሚባሉት የኤም23 አማጺያን በምስራቅ ኮንጎ የምትገኘውን ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ቡካቩን መቆጣጠራቸውን ሮይተርስ የጸጥታ መንጮችንና እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።
አማጺ ቡድኑ ባለፈው ጥር ወር መጨረሻ የጎማ ከተማን ከያዘ ወዲህ ወደ ደቡብ ኪቩ ግዛት ሲገሰግስ ቆይቷል።
የቡካቩ መያዝ የመረጋገጥ ከሆነ ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ከ2022 ወዲህ አማጺያኑ የተቆጣጠሩት ቦታ መስፋቱን የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የኤም23 ቃል አቀባይ ዊሊ ንጎማ ቡድኑ ከተማ ውስጥ መግባቱን ለሮይተርስ ተናግሯል። ዘገባው ከኮንጎ ጦር ምላሽ አለማግኘቱን ጠቅሷል።
አንድ ለሮይተርስ ምስክርነቱን የሰጠ እማኝ " እቤት ነው ያለሁት፣ የኤም23 አማጺያንን በከተማው ውስጥ አይቻለሁ" ሲል ተናግሯል።
ደሞክራሲያዊ ረፐብሊክ ኮንጎ ጎረቤቷን ሩዋንዳን የኤም23 አማጺያንን በማስታጠቅና በመርዳት ክስ እያቀረበች ነው። ግጭቱ እንዲቆም አለምአቀፍ ጥሪዎች ቢደረጉም እስካሁን አልተሳካም። በአዲስ አበባ እተየካሄደ ያለው የአፍሪካ መሪዎች ጠቅላላ ጉባኤ ይህን ግጭት መነጋገሪያ አጀንዳ አድርጎታል።