ፈረንሳይ ለፕሬዝዳንት ፑቲን የሰጠቻቸውን የክብር ሽልማት ልትነጥቅ እንደምትችል ገለጸች
ፕሬዝዳንት ማክሮን ሽልማቱን ለመንጠቅ "ትክክለኛውን ጊዜ" እየጠበኩ ነው ብለዋል
ፑቲን በፈረንጆቹ 2006 የፈረንሳይ “ግራንድ-ክሮክስ ዴ ላ ሌጌዎን ዲ ሆነር” የክብር ሽልማት መቀባላቸው ይታወሳል
ፈረንሳይ ለፕሬዝዳንት ፑቲን የሰጠቻቸውን የክብር ሽልማት ልትነጥቅ እንደምትችል ገለጸች
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፈረንሳይ ለሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲንን የሰጠቸውን ከፍተኛ የሀገሪቱ የክብር ሽልማት ልትነጥቅ መሆኑ ተናገሩ፡፡
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን የሁለቱም ሀገራት ግንኙነት የተሻለ ምእራፍ ላይ ነው በተባለበት በ2006 ከወቅቱ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ዣክ ረኔ ሺራክ “ግራንድ-ክሮክስ ዴ ላ ሌጌዎን ዲ ሆነር” የክብር ሽልማት መቀበላቸው ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጅ አሁን ሩሲያ በዩክሬን ላይ የጀመረችውን ወታደራዊ ዘመቻ ተከትሎ ፈረንሳይ ሞስኮው መሪ የሰጠችውን ክብር ልትነጥቅ መሆኑ እየተገለጸ ነው፡፡
ጉደዩ አነጋጋሪ የሆነው ፕሬዝዳንት ማክሮን ለዩክሬኑ አቻቸው ቮሎዲሚር ዘለንስኪን እሮብ እለት ከፍተኛ የክብር ሽልማት መስጠታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
በዚህም ለሁለት ተቃራኒ መሪዎች ተማሳሳይ ሽልማት ስለሰጠችው ፈረንሳይ የተጠየቁት ማክሮን፤ የፑቲን የሜዳሊያ ጥያቄ "ምሳሌያዊ ግን ጠቃሚ" መሆኑን አምነዋል።
ፓሪስ ለፑቲን የሰጠችውን የክብር ሽልማት ለመግፈፍ " ትክክለኛውን ጊዜ" እየጠበኩ ነውም ነው ያሉት ማክሮን፤ የአውሮፓ መሪዎች ወደ ዩክሬን የሚደርሰውን የጦር መሳሪያ አቅርቦት ለማሳደግ ከተመከረበት ጉባኤ በኋላ ባደረጉት ንግግር፡፡
ውሳኔው “ዛሬ የወሰንኩት ውሳኔ አይደለም” ሲሉም መናገራቸውም ፍራነስ-24 ዘግቧል፡፡
ፑቲን በዩክሬን ላይ የጀመሩት ወታደራዊ ዘመቻ ፈረንሳይን ጨምሮ መላውን የምዕራቡ ዓለም ሀገራት የተቃወሙት ጉዳይ ነው፡፡
ሀገራቱ ከመቃወም በዘለለ በሞስኮ ላይ በርካታ የኢኮኖሚ ማችቀቦች መጣላቸውም ይታወቃል፡፡