መዲናን የረገጠ ሁሉ የማይረሳቸው ሼክ ኢስማኤል አል ዛይም አረፉ
ሼክ ኢስማኤል ባለፉት 40 አመታት ለሀጂና ኡምራ ተጓዦች ቴምር፣ ቡና እና ሻይ በነጻ ሲያቀርቡ ቆይተዋል
በሶሪያ ሃማ የተወለዱት “አቡ አል ሳባ” በለጋስነታቸው ታዋቂነትን አትርፈው ነበር
ሶሪያዊው ሼክ ኢስማኤል አል ዛይም አቡ አል ሳባ በ96 አመታቸው አረፉ።
የሳኡዲ አረቢያዋን መዲና ከተማ የረገጠ ሁሉ ያውቃቸዋል አልያም ደግነታቸውን ሰምቷል የሚባልላቸው ሼክ ኢስማኤል የማይነጥፍ ችሮታቸው እስከህልፈታቸው ድረስ ዘልቋል።
ለሀጂና ኡምሯ ከተለያየ የአለም ክፍል የመጣ ሙስሊምም ሆነ መዲናን የሚጎበኝ የሌላ እምነት ተከታይ የሼህ ኢስማኤልን የነጻ በረከት ተቋድሷል ነው የሚባለው።
እኝህ አባት ባለፉት 40 አመታት በቀን ከ300 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ውሃ፣ ቡና፣ ወተት፣ ሻይ፣ ዳቦና ቴምር በነጻ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
አንድም ቀን የምሰጠው አጥቼ አላውቅም የሚሉት ሼህ ኢስማኤል፥ ለበጎ ስራቸው ከማንም ክፍያ እንደማይጠይቁ ለሳኡዲ መገናኛ ብዙሃን ተናግረው ነበር።
የነብዩ ቀብር ከሚገኝበት መስጂድ አጠገብ በፕላስቲክ ወንበራቸው ላይ ተቀምጠው ጎብኝዎችን በፈገግታ እየተቀበሉ ማስተናገድ በፈጣሪያቸው የሚያስገኝላቸውን በረከት ብቻ ነበር የሚያስቡት።
የአራት አስርት አመት ልግስናቸውና በጎ ምግባራቸው መዲናን በረገጠ ሁሉ ተወዳጅ ያደረጋቸው ሼህ ኢስማኤል አል ዛይም በሶሪያዋ ሃማ ከተማ መወለዳቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።
በርካቶች “አቡ አል ሳባ” እያሉ የሚጠሯቸው አባት በህመም ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
aXA6IDE4LjExOS4xMTguOTkg
ejasoft island