አለምአቀፉ የትምህርት እና አየር ንብረት ጉባኤ ተካሄደ
ከኮፕ28 ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሄደው ይህ አለምአቀፍ የሪዋየርድ የትምህር እና አየር ንብረት ጉባኤ 100ዐ ሰዎች ተሳትፈውበታል
ስብሰባው 22 ሚኒስትሮችን፣ 28 ዋና ስራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም ከ76 ሀገራት የተውጣጡ ተናጋሪዎች ያሳተፈ በአለም የመጀመሪያው የትምህርት እና አየር ንብረት ጉባኤ ነው
አለምአቀፉ የትምህርት እና አየር ንብረት ጉባኤ ተካሄደ።
ከኮፕ28 ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሄደው ይህ አለምአቀፍ የሪዋየርድ የትምህር እና አየር ንብረት ጉባኤ 100ዐ ሰዎች ተሳትፈውበታል።
የኮፕ28 ስብሰባ እየተካሄደ በሚገኝበት የዱባይ ኤክስፖ ውስጥ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ትምህርት የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ወሳኝ ሚና እንዳለው መግባባት ላይ ተደርሷል።
የኢምሬትስ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ስብሰባው 22 ሚኒስትሮችን፣ 28 ዋና ስራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም ከ76 ሀገራት የተውጣጡ ተናጋሪዎች ያሳተፈ በአለም የመጀመሪያው የትምህርት እና አየር ንብረት ጉባኤ ነው።
የሪዋየርድ ጉባኤ ትምህርት የአየር ንብረት ለውጥ በመዋጋት ረገድ የሚኖረውን ሚና ለማጠናከር ከተለያዩ ዘርፎች ያሉ ባለድርሻ አካላትን ስብስቧል።
ጉባኤው ሀሉንም አጋሮች በአንድ ጥላ ስር በማሳተፍ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ የትምህርትን ሚና ለማጉላት እንደሚጥር ገልጿል።
በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው አለምአቀፉ የአየር ንብረት ስብሰባ ላይ 198 ሀገራት ተወክለዋል፣ የተለያዩ ስምምነቶችም ደርሰዋል።