ኮሮና ቫይረስ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በአፍሪካ ከ470 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ሞተዋል ተባለ
በዓለማችን በአንድ ዓመት ውስጥ በወባ በሽታ ከሞቱ 627 ሺህ ዜጎች ውስጥ 75 በመቶው አፍሪካዊ ናቸው
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት የወባ በሽታ ትኩረት እንዲነፈገው አድርጓል ተብሏል
ኮሮና ቫይረስ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በአፍሪካ ከ470 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ሞተዋል ተባለ፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት የኮሮና ቫይረስ መከሰት ለወባ በሽታ ተሰጥቶት የነበረው ትኩረት እየቀነሰ እንዲመጣ አድርጎታል ብሏል፡፡
በዚህም ምክንያት በፈረንጆቹ 2020 በወባ በሽታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር በ2019 ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በ69 ሺህ እንዲጨምር ማድረጉን የተቋሙ ዓመታዊ የወባ ሪፖርት ያስረዳል፡፡
በዚሁ ተመሳሳይ ዓመት በዓለማችን 627 ሺህ ሰዎች በወባ በሽታ የሞቱ ሲሆን ከሟቾቹ ውስጥ ሁለት ሶስተኛው ወይም ከ470 ሺህ በላይ ያህሉ አፍሪካዊያን መሆናቸውን ድርጅቱ ገልጿል፡፡
የኦሚክሮን ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ሆስፒታሎቿን ዝግጁ ማድረጓን ደቡብ አፍሪካ አስታወቀች
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተወሰዱ የእንቅስቃሴ ገደብ እና ሌሎች እርምጃዎች በወባ በሽታ ከሞቱ ዜጎች መካከል የሲሶውን ድርሻ አበርክቷልም ብሏል የዓለም ጤና ድርጅት በሪፖርቱ፡፡
ይህ በዚህ እንዳለም የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካ 224 ሺህ ዜጎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን በዚሁ ቫይረስ ምክንያት የሚሞቱ ዜጎች በመጨመር ላይ ይገኛል፡፡
የወባ በሽታ ስርጭት በ2020 ዓመት በአፍሪካ በተለይም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በረሃ በታች ባሉ አገራት በ12 በመቶ መጨመሩን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡