ማላዊ ኮሮናን ለመከላከል የሚውለውን በጀት አባክነዋል ያለቻቸውን ሚኒስትር አባረረች
ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ እስካሁን 19 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል
ማላዊ ለኮሮና መከላከያ ከተመደበው በጀት ውስጥ 8 ሚሊዮን ዶላር መመዝበሩን አስታውቃለች
የማላዊ ፕሬዘዳንት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተመደበ በጀትን አባክነዋል በሚል የሰራተኛ ጉዳዮች ሚኒስትራቸውን አባረሩ።
ማለዊ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚል ከበጀተችው ውስጥ 8 ሚሊዮን ዶላር ገደማ መመዝበሩን ገልጻለች።ከምዝበራው ጋር በተያያዘ እስካሁን በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ቁጥር 19 ደርሷል።
በቅርቡ በተደረገ ምርጫ አሸንፈው ስልጣን የያዙት ላዛሩስ ቻኩዌራ የሰራተኛ ሚኒሰትሩን ማላዊ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በሚል የበጀተችውን ገንዘብ አባክነዋል በሚል ከስልጣን አሰናብተዋል።
ፕሬዘዳንቱ የበጀት ኦዲት እንዲደረግ ካደረጉ በኋላ ሚኒስትሩ 7 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ጉድለት እንደተገኘባቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
የበጀት ጉድለቱን ተከትሎ ከሚኒስትሩ ስልጣን መነሳት በተጨማሪ ከ12 በላይ ከፍተኛ ባለሙያዎችም በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
የበጀት ጉድለት ምርመራው አሁንም የቀጠለ ሲሆን ተጨማሪ ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ሊውሉ እንደሚችሉ ፕሬዘዳንት ቻኩዌራ ተናግረዋል።
የሰራተኛ ሚኒስትሩ ከ613 ሺህ ክዋቻ (የማላዊ መገበያያ ገንዘብ) ከህግ ውጪ ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ከተመደበው በጀት ላይ ወደ ደቡብ ተመላልሰዋል በሚልም ክስ ቀርቦባቸዋል።
ይሁንና እኝህ ሚኒስትር በመንግስታቸው ክስ መደንገጣቸውን ለሮይተርስ ተናግረዋል።
በማላዊ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተመደበ ገንዘብን መዝብረዋል በሚል ተጠርጥረው በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ቁጥር 19 የደረሰ ሲሆን በአስሩወስጥ ጋዜጠኞች፤የካቢኔ አባላት እና ሌሎች ሰራተኞች ይገኙበታል።
በማላዊ እስከ ዛሬ ድረስ ከ33 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 1 ሺህ 138 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።