የማላዊ ፕሬዝዳንት የማዕድን ሚኒስትሩን እና ሌሎች ሹመኞችን ከሥራ አገዱ
ፕሬዝዳንቱ የሰራተኛ ሚኒስትርን ጨምሮ 19 የመንግስት ባለስልጣናትን ከኃላፊነት ማንሳታቸው ይታወሳል
ፕሬዝዳንቱ አንድ የካቢኔ አባልና አማካሪያቸውን ከኃላፊነት ያነሱት ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ነው ተብሏል
የማላዊ ፕሬዝዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ የሀገሪቱን ማዕድን ሚኒስትር እና አማካሪያቸውን ከስራ ማሰናበታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አንድ የካቢኔ አባል፤ አማካሪያቸውን ሃላፊና አንድ ሌላ ግለሰብ ከኃላፊነት እንዲነሱ ያዘዙት ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ከስልጣን የተነሱት የማዕድን ሚኒስትሩ ኔውተን ካምባላ፤ የፕሬዝዳንቱ የስትራቴጅ አማካሪ ቻይማ ባንዳ እና የሕግ አውጭው ኢኖች ቺሃና መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
አሁን ላይ ከስልጣን እንዲነሱ በፕሬዝዳንቱ ውሳኔ የተላለፈባቸው እነዚህ ባለስልጣናት የሙስና ክስ እንደሚቀርብባቸው ተገልጿል፡፡ ባለስልጣናቱ የሀገሪቱ የዘይት ኮንትራት አግባብ ላልሆነ ድርጅት እንዲሰጥ አድርገዋል በሚል መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡ ከስልጣን የተነሱት ሶስቱም የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስተያየት ለመስጠት መቆጠባቸውም ተዘግቧል፡፡
የማዕድን ሚኒስትሩ ካምባላ በ20 ዓመታት የሀገሪቱ ታሪክ በስልጣን ላየ እያሉ የተያዙ ያደርጋቸዋል ነው የተባለው፡፡ የማላዊ ፕሬዝዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ ባለፈው ሚያዚያ ከሙስና ጋር በተያያዘ የሰራተኛ ሚኒስትርን ጨምሮ 19 የመንግስት ባለስልጣናትን ከኃላፊነት ማንሳታቸው ይታወሳል፡፡
ከስልጣን እንደተነሱ የተገለጸው የፕሬዝዳንቱ የስትራቴጅ አማካሪ ቻይማ ባንዳ እስካሁን ለስልጣናቸው እንዳልተነሱ ገልጸዋል፡፡ ባለስልጣናቱ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተገኘውን ፈንድ አጭበርብረዋል በሚል ከኃላፊነታቸው መነሳታውም በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡