ቦይንግ ኩባንያ ሙሉ ለሙሉ በታዳሽ ሀይል የሚሰሩ አውሮፕላኖችን እንደሚያመርት አስታወቀ
በታዳሽ ሀይል የሚበሩ አውሮፕላኖችን ማምረት ቀጣዩ የአቪዬሽን ኢንዱትሪ መወዳደሪያ ይሆናል ተብሏል
ነዳጅን በመጠቀም የሚበሩ አውሮፕላኖች ብዙ የዓለማችን አየር መንገዶችን ከውድድር እያስወጣ ነው ተብሏል
ቦይንግ ኩባንያ ሙሉ ለሙሉ በታዳሽ ሀይል የሚሰሩ አውሮፕላኖችን እንደሚያመርት አስታወቀ፡፡
የዓለማችን ግዙፉ የአቪየሺን ቦይንግ ኩባንያ የሆነው ቦይንግ ከፈረንጆቹ 2030 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ በታዳሽ ሀይል የሚበሩ አውሮፕላኖችን ለደንበኞቼ አቀርባለሁ ብሏል፡፡
የኩባንያው የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት ኮልጌት ጋታ ኡራ ከአልዓይን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በታዳሽ ሀይል የሚሰሩ አውሮፕላኖች ጉዳየ ቀጣዩ የአቪየሺን ኢንዱስትሪዎች ዋነኛ መፎካከሪያ ይሆናል ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አክለውም አሁን ላይ ነዳጅን በመጠቀም የሚበሩ አውሮፕላኖች ብዙ የዓለማችን አየር መንገዶችን ከውድድር እያስወጣ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
- ህንድ ከታዳሽ ሃይል 500 ጊጋዋይት ሃይል ለማመንጨት እየሰራች መሆኑ የሚደነቅ ነው - አል ጀበር
- የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዛይድ 2023ን "የዘላቂነት ዓመት" በሚል አወጁ
ቦይንግ ኩባንያ ከፈረንጆቹ 2030 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ታዳሽ ሀይልን የሚጠቀሙ አውሮፕላኖችን ለማምረት በስድስት አህጉራት ፕሮጀክቶችን በመተግበር ላይ እንደሆነም ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል፡፡
ቦይንግ እየተገበራቸው ካሉ የታዳሽ ሀይል ፕሮጀክቶች መካከልም በደቡብ አፍሪካ ከትንባሆ ተክል፣ በብራዚል የሸንኮራ ሀይል ማመንጨት በተባበሩት አረብ ኢምሬት ከኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶች እንዲሁም በሌሎች ሀገራት ደግሞ ከመኖሪያ ቤቶች በሚወጡ ተረፈ ምርቶች ታዳሽ ሀይል የማመንጨት አማራጮችን እየተተገበሩ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ኩባንያው እየተከተላቸው ካሉ የታዳሽ ሀይል አማራጮች ውስጥ የሰው ልጆችን ፍላጎት በማይጋፉ እና የአየር ንብረት መዛባትን በማያስከትሉ መንገድ እንደሆኑም ፕሬዝዳንቱ በቃለ መጠይቃቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡
ቦይንግ ከዚህ በተጨማሪም ለታዳሽ ሀይል ልማት የሚሆኑ ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ጎን ለጎን እያለማ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን ከዚህ በፊት በኩባንያው ተመርተው በነዳጅ እየሰሩ ያሉ አውሮፕላኖች በከፊል ወደ ታዳሽ ሀይል ሊቀየሩ የሚችሉባቸውን መንገዶችንም እንደሚከተል ገልጿል፡፡
ባለፉት ሳምንታት የኢምሬት አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 77 አውሮፕላን ሙሉ ለሙሉ በታዳሽ ሀይል የታገዘ የበረራ ሙከራ ማድረጉ ኩባንያው ለያዘው እቅድ ውጤታማነት ፈር ቀዳጅ ይሆናልም ተብሏል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፈረንጆቹ 2050 ላይ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቅ በካይ ጋዝ መጠንን ዜሮ የማድረስ እቅድ የነደፈ ሲሆን በብዙ መስኮች ይህን እቅድ ማሳካት የሚያስችሉ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡
ብዙ ሀገራት እና ኩባንያዎች በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ምርቶችን በመፈብረክ ላይ ሲሆኑ ተሸከርካሪዎች ለዚህ ማሳያዎች ናቸው፡፡