የአረብ ኢምሬትሱ የኮኘ28 ስብሰባ ስኬታማ እንደሚሆን እንተማመናለን- የማልዲቭስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ሚኒስትሩ በአየርንብረት ለውጥ ጉዳዮ በማልዲብስ እና በአረብ ኢምሬትስ መካከል ጠንካራ ትብብር አለ ብለዋል
በህንድ ወቅያኖስ ዳርቻ ያለችው ማልዲቭስ የአየር ንብረት ለውጥ ስጋት ደቅኖባታል ብለዋል ሚኒስትሩ
የማልዲቭስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላህ ሻሄድ የማልዲቭስ እና የህዝቧ የወደፊት እጣፋንታ በመጭው ህዳር በዱባይ በሚከበረው የኮፕ28 ስብሰባ ስኬት የእንደሚወሰን ገልጸዋል።
አብዱላህ ሻሄድ ለኢምሬትስ ኒውስ ኤጀንሲ(ዋም) በላኩት መግለጫ የአየር ንብረት ለውጥ የህልውና ጉዳይ መሆኑን እና ማልዲቭስን ጨምሮ በብዙ ሀገራት ላይ አደጋ መደቀኑን ተናግረዋል።
"በአረብ ኢምሬት መሪነት የሚካሄደው የኮፕ 28 ስብሰባ የሚፈለገውን ውጤት እንደሚያመጣ እንተማመናለን" ሲሉ ሚኒስትሩ አክለዋል።
በኮፕ 28 ስብሰባ ፕሬዝደንት ዶክተር ሱልጣን ቢን አህመድ አል-ጀባር እንደሚተማመኑ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ የስብሰባው ፕሬዝደንት የተለያዩ ሀሳቦች ወደ አንድ እንዲመጡ፣ ለህዝብ ህልውና ዋስትና የሚሰጡ ውጤታማ ውሳኔዎች እንዲወሱ ጫና የማድረግ ሚና እንዳቸውም ገልጸዋል።
በህንድ ወቅያኖስ ዳርቻ ያለችው ማልዲቭስ የአየር ንብረት ለውጥ ስጋት ደቅኖባታል ብለዋል ሚኒስትሩ።
ሚኒስትሩ እንዳሉት ማልዲቭስ ብቸኛ ተጠቂ ባትሆንም ቀዳሚ ተጠቂ መሆኗን ገልጸዋል። በፖሪስ ስብሰባ አለም አቀፍ ሁኔታን የዳሰሰው የአየር ንብረት ጉባዔ በዚህኛው ስብሰባ ተጨባጭ እርምጃዎችን ይወስዳል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ በአየርንብረት ለውጥ ጉዳዮ በማልዲብስ እና በአረብ መካከል ጠንካራ ትብብር አለ ብለዋል።