ሩሲያ የማዕድን ፍለጋዋን ከአንድ ወር በኋላ ትጀምራለች ተብሏል
ሩሲያ በማሊ የሊቲየም እና ነዳጅ ፍለጋ ልታደርግ መሆኗን ገለጸች፡፡
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ማሊ ከምዕራበዊን በተለይም ከቀደሞ ቅኝ ገዢዋ ማሊ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራት፡፡
በኮለኔል አስሚ ጎይታ የሚመራው ወታደራዊ ክንፍ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ከፈረንሳይ ጋር ያለውን ግንኙነት በማቋረጥ ከሩሲያ ጋር ጥብቅ ወዳጅነት መስርቷል፡፡
ሩሲያ እና ማሊ በየጊዜው ትብብራቸው እያደገ የመጣ ሲሆን አሁን ደግሞ በዓለም ላይ ተፈላጊ ከሆነው ማዕድን ውስጥ ዋነኛው የሆነው ሊቲየም ለማውጣት ከሞስኮ ጋር ስምምነት ፈጽማለች፡፡
ማሊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለመስራት ዋነኛ ግብዓት የሆነው ሊቲየም እንዳላት ቢታወቅም እስካሁን ይህን ሀብት በማውጣት ለገበያ ማቅረብ ሳትችል ቆይታለች፡፡
በአፍሪካ በአደገኛ ሁኔታ እየጨመረ የሚገኝው ሕገ ወጥ የሰውነት ክፍሎች ሽያጭ
ሀገሪቱ ከሩሲያ ጋር በደረሰችው ስምምነት መሰረተም ከአንድ ወር በኋላ የሞስኮ ማዕድን ፍለጋ ባለሙያዎች ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል፡፡
ሁለቱ ሀገራት ከሊቲየም ባለፈ የነዳጅ ሀብት ፍለጋ ስምምነት መፈራረማቸውን የማሊ የኢኮኖሚ እና ገንዘብ ሚኒስትሩ አሉሴኒ ሳኑ ተናግረዋል፡፡
የማሊ ኢነርጂ እና ኢንቨስትመንት ሚኒስትሮች ወደ ሞስኮ አቅንተው የማዕድን ፍለጋ ስምምነት ከሩሲያ ባለስልጣናት ጋር እንደተፈራረሙ አናዶሉ ዘግቧል፡፡
ማሊን ጨምሮ ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ ከምዕራባዊን ሀገራት ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማቋረጥ ከሩሲያ ጋር ጥብቅ ግንኙነት የመሰረቱ ሀገራት ናቸው፡፡
ሶስቱ ሀገራት ከአፍሪካ ህብረት አባልነት የታገዱ ሲሆን በራሳቸው ፈቃድ ደግሞ ከምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ አባልነታቸው ለቀዋል፡፡