ስደተኛው በድንገት በጥፊ የመታት ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆና ተገኘች
ለእስር የተዳረገው ይህ ስደተኛ በጥፊ የመታኋት ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር መሆኗን አላወኩም ብሏል
በወቅቱ ሰክሬ ነበር የሚለው ይህ ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን ተገዶ ሀገር እንዲለቅ ሊደረግ እንደሚችል ይጠበቃል
ስደተኛው በድንገት በጥፊ የመታት ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆና ተገኘች፡፡
ስሙ ለደህንነቱ በሚል ያልተጠቀሰው አንድ ፖላንዳዊ በኮፐንሀገን ጎዳናዎች ላይ እየተጓዘ እያለ ከፊት ለፊቱ የምትመጣ ሴትን በጥፊ ይመታል፡፡
በፈጸመው ድርጊት ወዲያውኑ በፖሊስ የተያዘው ይህ ሰው እንደ ቀልድ እጁን የሰነዘረባት ሴት የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበረች፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ሜት ፍሬድሪክሰን በወቅቱ ለአውሮፓ ህግ አውጪ ምክር ቤት ለመመረጥ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ነበር ወደ ሀገሪቱ መዲና ኮፐንሀገን ጎራ ያሉት፡፡
በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ ባልጠበቁት መልኩ በጥፊ የተመቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ፍሬድሪክሰን በሁኔታው ክፉኛ ደንግጠው እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሯ የምርጫ ቅስቀሳቸውን ለማቋረጥ የተገደዱ ሲሆን ከምርጫውም ራሳቸውን ለማግለል ተገደዋል፡፡
በደረሰባቸው ድብደባ የከፋ የጤና ጉዳት ያልደረሰባቸው ጠቅላይ ሚኒስትሯ ፖሊስ ባጣራው መሰረት ግለሰቡ ፖላንዳዊ ስደተኛ እንደነበር ተደርሶበታል፡፡
የ14 ሚሊየን ብር ሎተሪ የወጣለት እድለኛው ስደተኛ በአውሮፓ
ይህ ስደተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደተናገረው በወቅቱ ምን እንደፈጸመ እንደማያስታውስ እና ሰክሮ እንደነበር አስረድቷል ተብሏል፡፡
ይህን ተከትሎም ይህ ስደተኛ እስር እና በግዳጅ ከዴንማርክ ወደ ፖላንድ የመባረር እጣ እንደሚጠብቀው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የ46 ዓመቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜት ፍሬድሪክሰን ከፈረንጆቹ 2019 ዓመት ጀምሮ የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው፡፡