በ9 ቀናት ውስጥ ለፖሊስ ከ2 ሺህ ጊዜ በላይ የደወሉት አዛውንት ዘብጥያ ወርደዋል
ጃፓናዊው ግለሰብ ፖሊሶችን ለመሳደብ 27 ስአታት የወሰዱ የስልክ ጥሪዎችን አድርገዋል ተብሏል
ግለሰቡ ደውለው የሚሳደቡበት ምክንያት ግን አሁንም ሚስጢራዊ ነው
ጃፓናዊው አዛውንት ፖሊሶችን ስልክ በመደወ አጨናንቀዋቸው ሰንብተዋል።
የ67 አመቱ ስሙ ያልተጠቀስ አዛውንት በዘጠኝ ቀናት ውስጥ ብቻ 2 ሺህ 60 ጊዜ ወደ ፖሊሲ ደውለዋል።
አዛውንቱ አደጋ ገጥሟቸው አስቸኳይ ድጋፍ ፈልገው ግን አይደለም።
በየቀኑ በአማካይ 229 ጊዜ ወደ ፖሊሶች የደወሉት ለመሳደብ ነው።
ሲያትማ በተሰኘች ከተማ የሚኖረው አዛውንድ ፖሊሶችን "የታክስ ሌቦች" የሚሉና ሌሎች ፀያፍ ስድቦችን መሳደቡን የከተማዋ ፓሊስ ገልጿል።
አጠቃላይ የደወሉት ደቂቃ ርዝማኔም 27 ስአት የሚወስድ መሆኑን ነው የሲያትማ ፓሊስን ጠቅሶ ኦዲቲ ሴንትራል ያስነበበው።
ፓሊስ አዛውንቱን በቤታቸው በቁጥጥር ስር አውሏቸው የፀጥታ ሰራተኞችን ስራ በማወክና ሰብአዊ ክብራቸውን በስድብ በማንቋሸሽ ወንጀል ከሷቸዋል።
"አንድ ቀን ቤቴ ድረስ መጥታችሁ እንደምትይዙኝ አውቅ ነበር" ያሉት አዛውንት ለፖሊስ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተባባሪ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።
ጃፓናዊው በዘጠኝ ቀናት ውስጥ ከ2 ሺህ ጊዜ በላይ ያስደወላቸው ሚስጢር እስካሁን አልተፈታም።
የኋላ ዶሴያቸው ሲፈተሽም ከዚህ ቀደምም ደጋግመው ለፖሊስ እንደሚደውሉ መረጋገጡ ለምን ይሆን ያለመታከት የሚደውሉት የሚለውን አጓጊ አድርጎታል።
አዛውንቱ በጃፓን ማህበራዊ ገፆችም ድጋፍና ነቀፌታን አስተናግደዋል።
"ለስንት አጣዳፊ ጉዳይ የሚፈለግ የፓሊስ የስልክ መስመርን ለረጅም ጊዜ መያዝ ምን ይሉት እሳቤ ነው" የሚሉት ወገኖች ሲነቅፏቸው፤ ምንም ቢሆን ለያዙት አላማ ያለመታከት መታገላቸውን ያወደሱትም ደግፈዋቸዋል።
aXA6IDE4LjE5MS4yMzkuMTIzIA== ejasoft island