“ምንም ሳልሰራ ደመወዝ እየተከፈልኝ ነው” ያለው ግለሰብ ለተቋሙ ቅሬታ አስገብቷል
በርካቶች ስራን በሚያማርሩበት በዚህ ወቅት አየርላናደዊው ግለሰብ “ሳልሰራ ደመወዝ እየተከፈልኝ ነው” ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል
በዓመት 130 ሺህ ዶላር ደሞዝ የሚከፈለው ግለሰቡ “ቢሮ ገብቼ ጋዜጣ ከማንበብና ምሳ ከመብላት ውጪ ስራ የለኝም” ብሏል
አየርላንዳዊው ግለሰብ “ምንም ሳልሰራ ደመወዝ እየተከፈልኝ ነው” ሲል ለተቋሙ ቅሬታ ማስገባቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
በአየርላንድ ብሄራዊ የባቡር ትራንስፖርት ውስጥ የፋይናንስ ኃላፊ የሆነው ግለሰቡ በዓመት 130 ሺህ ገደማ የአሜሪካ ዶላር እየተከፈለው ነው የሚሰራው።
ሆኖም ግን “ቢሮ ውስጥ ምንም ስራ የለኝም፤ ቢሮ ገብቼ ጋዜጣ ለማንበብ እና ምሳ ለመብላት ብቻ ነው ደመወዝ እየተከፈለኝ ያለው” ብሏል።
ምንም ነገር ሳይሰሩ ደመወዝ መቀበል አብዛኛውን ሰው የሚያማርረው አይመስልም ነገር ግን በአይሪሽ ባቡር ውስጥ የፋይናነስ ኃላፊ ለሆነው ለዴርሞት አላስታይር ሚልስ ግን መገለል መስሎ ታይቶታል ብሏል ኦዲቲ ሴንተራል በዘገባው።
- የዓለማችን ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋይ መሪ ማን ነው?
- አሁን ባለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ዝቅተኛው የተቀጣሪ ደመወዝ ለጊዜው 6 ሺህ 800 ብር መሆን አለበት- የምጣኔ ሀብት ባለሙያ
የፋይናናስ ሥራ አስኪያጁ በፈረንጆቹ በ2014 የኩባንያውን የሂሳብ አያያዝ በተመለከተ መረጃ አቀብሏል ከተባለ በኋላ ቀስ በቀስ ከስራ ውጪ የተደረገ ሲሆን፤ አሁን አብዛኛውን ቀኑን ምሳ በመመገብ እና ጋዜጦችን በማንበብ የሚያሳልፍበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል።
ይህ ሁሉ ሲሆን አሁንም በየወሩ መደበኛ ደመወዙን እየተቀበለ መቀጠሉም ነው የተነገረው።
ሚልስ ስለ ስራው እና ውሎው ሲናርም፤ ጠዋት ላይ “ታይምስ እና ዘ ኢንዲፕነዴንት” የተባሉ ሁለት ጋዜጦችን እንዲሁም ሳንድዊች እገዛለው፤ ወደ ቢሮ ገብቼ የተላከልኝ ሜይል ካለ ብዬ ኢ ሜይል ለመመለስ ብከፍትም ምን አይነት መልእክት የለም” ብሏል።
“ስለዚህ ቀኑን ሙሉ ቁጭ ብዬ የገዛዋቸውን ጋዜጦች በማንበብ እና ሳንድዊች በመብላት አሳልፋሁ” ያው ሚልስ “ጠዋት 4፡30 አካባቢ ከስራ ጋር የተገናኘ ኢሜይል ካለ እና የሚሰራ ነገር ካለው እሱን ሰርቼ እመልሳለሁ፤ እንዲህ አይነት ስራ በሳምንት አንዴ ብቻ ባገኝ ነው” ሲልም ተናግሯል።