ለአንድ ቀበሌ ነዋሪዎች በበጎ ፈቃደኝነት ድልድይ የሰራው ሰው ታሰረ
መንግስት ድልድዩን ካፈረሰ በኋላ ደረጃውን ጠበቀ አዲ ድልድይ እገነባለሁ ቢልም እስካሁን እውን አልሆነም
ግለሰቡ ከ18 ሺህ በላይ ዶላር ወጪ በማድረግ ድልድይ ቢሰራም የሁለት ዓመት እስር ተላልፎበታል
ለአንድ ቀበሌ ነዋሪዎች በበጎ ፈቃደኝነት ድልድይ የሰራው ሰው ታሰረ፡፡
የቻይናዋ ዜንሊን የተሰኘችው መንደር በሰሜናዊ የሀገሪቱ ገጠራማ ክፍል የምትገኝ የመሰረተ ልማት ችግር ያለባት ቀበሉ ነች፡፡
ታኦር የተሰኘው ወንዝ ደግሞ ይህችን መንደር ከሌሎች አጎራባች ቀበሌዎች ጋር እንዳትገናኝ ያደረገ ግዙፍ ወንዝ ነው፡፡
የመንደሩ ነዋሪዎች ወደ አጎራባች ቀበሌዎች ለመጓዝ በትንሹ 70 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሁዋንግ ደዪ የተባለው የዚችው ቀበሌ ነዋሪ የሆነ ባለጸጋ ከ18 ሺህ ዶላር በላይ ገንዘብ በማውጣት በወንዙ ላይ ድልድይ በመስራት አነስተኛ ገንዘብ እያስከፈለ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡
ቀስ በቀስም ይህ ድልድይ ሰዎችን ብቻ ከማሻገር ወደ ከባድ ተሸከርካሪዎችን ወደ ማሻገር ይሻሻላል፡፡
ሙሽሪት 3 ኪሎግራም ወርቅ ጥሎሽ ያገኘችበት አነጋጋሪው የቱርክ ሰርግ
ይሁንና የሀገሪቱ መንግስት ይህንን ግለሰብ ህገወጥ ስራ ሰርተሃል በሚል በቁጥጥርሰ ር ያዋለው ሲሆን የሁለት ዓመት እስርም ተላልፎበታል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በአንድ ግለሰብ አማካኝነት የተገነባውን ድልድይ ያፈረሰው ሲሆን አዲ ድልድይ ለህዝቡ እንደሚገነባ ቃል ገብቷል፡፡
የአካባቢው ሰውም ከዛሬ ነገ ቃል የተገባለት ድልድይ ይገነባል ብሎ ቢጠብቅም እስካሁን አለመገንባቱ ቅር እንዳሰኛቸው ተገልጿል፡፡
ጉዳዩ በመላው ቻይና ዋነኛ መነጋገሪያ አጀንዳ የሆነ ሲሆን ለእስር የተዳረገው ግለሰብ ባይኖር ኖሮ ህዝቡ ለከፋ እንግልት ይዳረግ ነበር፣ የድልድዩ መፍረስ ህዝቡ የለመደውን ቀላል ህይወት የበለጠ አክብዷል ብለዋል፡፡
ቀሪዎቹ ደግሞ በድልድዩ ላይ አደጋ ቢያጋጥም ለሚደርሰው ጉዳት ማን ሀላፊነት ይወስዳል የሚሉ አስተያየቶች በመሰንዘር ላይ ናቸው፡፡