ስትወሰልት ያገኛት ሚስቱን ያጋለጠው ባል የስድስት ወራት እስር ተፈረደበት
ባልየው ሚስቱን እጅ ከፍንጅ ከያዘ በኋላ ከውሽማዋ ጋር በመደራደር ገንዘብ ተቀብሏል ተብሏል
በሚስቱ ክስ የተመሰረተበት ባልም የተላለፈበትን የስድስት ወራት እስር ይግባኝ ቢልም እስከ መጨረሻው ያለው ፍርድ ቤት ውኔውን አጽንቷል
ስትወሰልት ያገኛት ሚስቱን ያጋለጠው ባል የስድስት ወራት እስር ተፈረደበት፡፡
ሉ የተሰኘው ቻይናዊ ሻንዶነግ በተሰኘችው በምስራቃዊ የቻይና የሚኖር ባለ ትዳር ሲሆን የአንድ ሴት ልጅ አባትም ነው፡፡
ባልየው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚስቱ ላይ የባህሪ ለውጥ ማየቱን ተከትሎ ነበር ክትትል ማድረግ የጀመረው፡፡
ባደረገው ክትትልም ሚስቱ ሊው ከተሰኘ ሌላ ወንድ ጋር እየማገጠችበት እንደሆነ ይገነዘባል፡፡
ባልየው ክትትሉን መቀጠሉን ተከትሎ ሚስቱ በከተማው ባለ አንድ ሆቴል ውስጥ ባለ መኝታ ክፍል ውስጥ ከወንድ ጋር እጅ ከፍንጅ ይዟታልም ተብሏል፡፡
በዚህ ወቅት በተደረገ ድርድር ሊው በፈጸመው ጥፋት ምክንያት 25 ሺህ ዩዋን ወይም 3 ሺህ 300 ዶላር ካሳ ለባልየው በመክፈል ጉዳዩን በስምምነት ይጨርሳሉ፡፡
ይሁንና ሚስትየው ቆይታ በባሏ ላይ ክስ የመሰረተች ሲሆን ክሱም ፍቅረኛዬን አንገላቶብኛል አስፈራርቶም ገንዘብ ተቀብሎታል የሚል መሆኑን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ከሌላ ወንድ ጋር ስትወሰልት በባሏ የተያዘች ሚስት ነጻነቴን ተጋፍቷል በሚል ክስ መሰረተች
ፍርድ ቤቱም ለባልየው የተከፈለውን የክፍያ ሰነድ እንደ ማረጋገጫ ካየ በኋላ በባልየው ላይ የስድስት ወር እስር ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡
ባልየው የተላለፈበት እስር ፍትሀዊ አለመሆኑን በመጥቀስ ይግባኝ ቢልም በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች ባልየው ትክክለኛ እና ስነ ምግባርን የተከተለ ነገር አላደረገም በሚል ውሳኔውን አጽንተዋል፡፡
ከአንድ ወር በፊት በተመሳሳይ ሚቱን የጠረጠረ ባል በመኖሪያ ቤቱ ሁነቶችን መከታተያ ድብቅ ካሜራ በመግጠም ሚስቱ ስትወሰልት ቢይዝም ሚስትየው ያለ ፈቃዴ በካሜራ ተከታትሎኛል የሚል ክስ መመስረቷን ተከትሎ ባልየው የሶስት ወራት እስር ተላልፎበት ነበር፡፡