ከሌላ ወንድ ጋር ስትወሰልት በባሏ የተያዘች ሚስት ነጻነቴን ተጋፍቷል በሚል ክስ መሰረተች
ሚስቱን የተጠራጠረው ባል በቤቱ ድብቅ ካሜራ ገጥሞ ሲከታተል ቆይቷል
የሰዎችን መብት ተጋፍቷል የተባለው ባልም የሶት ዓመት እስር ተፈርዶበታል
ከሌላ ወንድ ጋር ስትወሰልት በባሏ የተያዘች ሚስት ነጻነቴን ተጋፍቷል በሚል ክስ መሰረተች
ስማቸው ያልተጠቀሰው ባልና ሚስት ለዓመታት በትዳር ተጣምረው ሲኖሩ ቆይተዋል፡፡
ሁለት ልጆችን ያፈሩት እነዚህ ባልና ሚስትም ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በመካከላቸው አለመተማመን ይነግሳል፡፡
የሚስቱን የባህሪ ለውጥ ያየው ባልም በመኖሪያ ቤታቸው ሁለት ቦታዎች ላይ ድብቅ ካሜራ በመትከል ሁኔታዎችን መከታተል ይጀምራል፡፡
ብዙም ሳይቆይ ግን አንድ ሰው በአሳቻ ሰዓት ወደ መኖሪያ ቤቱ የሚገባ ሰው ይመለከታል፡፡ ይህ ሰውም የሚስቱ ውሽማ መሆኑን የተረዳው ባል ጉዳዩን በመያዝ ትዳሩን ለመፍታት ክስ ይመሰርታል፡፡
ክስ የተመሰረተባት ሚስትም ባሌ ያለ እኔ እውቅና በቤታችን ድብቅ ካሜራ በመትከል ነጻነቴን ተጋፍቷል ስትል ክስ መመስረቷ ተገልጿል፡፡
የታይዋን ፍርድ ቤትም በድብቅ ካሜራ ተክሎ ሚስቱን ሲሰልል የነበረው ባል ላይ የሶስት ዓመት እስር አስተላልፎበታል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ከባሏ ጋር ወሲብ በኮታ እና በክፍያ የምትፈጽመው ሚስት ትዳሯ እንዳይፈርስ ጠየቀች
እንደ ዘገባው ከሆነ ባልየው ፍርድ ቤቱ ሚስቱ በመወስለቷ ምክንያት ያቀረበውን የትዳር ይፍረስልኝ ጥያቄ ለምን ውድቅ እንዳደረገው አልተጠቀሰም፡፡
ባልየው በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ቢጠይቅም ተላፎበት የነበረው የሶስት ዓመት እስር እንዲጸና ተወስኖበታል፡፡
ጉዳዩ በመላው ታይዋን እና ቻይና መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን በርካቶችም በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸውን እያጋሩ ይገኛሉ፡፡