ከባሏ ጋር ወሲብ በኮታ እና በክፍያ የምትፈጽመው ሚስት ትዳሯ እንዳይፈርስ ጠየቀች
ሚስትየዋ ከባሏ ጋር ለምትፈጽመው ወሲብ በየጊዜው 15 ዶላር ስታስከፍል ቆይታለች ተብሏል
ወፍረሀል በሚል ክፍያ የምትጠይቀው ሚስት ባል ለፍቺ ሲጠይቅ ፈቃደኛ ሳትሆን ቀርታለች
ከባሏ ጋር ወሲብ በኮታ እና በክፍያ የምትፈጽመው ሚስት ትዳሯ እንዳይፈርስ ጠየቀች።
ሺዋን እና ሀኦ የተሰኙት ባልና ሚስት በፈረንጆቹ 2014 ላይ ነበር ጋብቻ የመሰረቱት።
ሁለት ልጆችን ያፈሩት እነዚህ ባልና ሚስቶች በተለይም ከ2017 ጀምሮ ግን ትዳራቸው ንፋስ ይገበዋል።
ጥንዶቹ በወቅቱ ያጋጠማቸው ችግር በወሲብ አለመጣጣም ሲሆን ችግራቸውን በውይይት ከመፍታት ይልቅ አባባሽ መፍትሔ እንደተከተሉ ተገልጻል።
ሚስት ባሏን ወፍረሀል በሚል በወር አንድ ጊዜ ብቻ ወሲብ የምትፈቅድለት ሲሆን ለዚህም 15 ዶላር እንዲከፍል አስገድዳለች ተብሏል።
ጉዳዩ የመረረው ባልም ፍቺ ለመፈጸም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዞት ቢሄድም ሚስት ችግሯን እንደምታስተካክል ቃል መግባቷን ተከትሎ ባል ክሱን አቋርጧል።
ይሁንና ከትንሽ ጊዜ በኋላ በድጋሚ ባል ወሲብ ከእሷ ጋር መፈጸም የሚችለው በወር ሁለት ጊዜ ብቻ እንደሆነ እና ለእያንዳንዱ ደግሞ 15 ዶላር እንዲከፍል ታስገድዳለች።
በሚስቱ ድርጊት የተበሳጨው ይህ ባል ጉዳዩን ድጋሚ ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ትዳሩ ላይጠገን ማብቃቱን እና ፍቺ እንደሚፈልግ ያስረዳል።
ለፍቺው ፍርድ ቤት የቀረበችው ሚስትም ትዳሯን እንደምትፈልገው ብትናገርም ችሎቱ ትዳሩ በፍቺ እንዲጠናቀቅ ውሳኔ ያሳልፋል።
ሚስት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ብትልም በድጋሚ ትዳሩ እንዲፈርስ የተላለፈውን ውሳኔ አጽንቷል ሲል ሳውዝ ቻይና ፖስት ዘግቧል።