የ45 ዓመቱ ግለሰብ “እስካሁን ለምን አላገባህም” እያለ በተደጋጋሚ የሚጠይቀውን ጉረቤቱን ገደለ
እንዲኔዢያዊው ግሰለሰብ ጎረቤቱን የገደለው በጥያቄው ተበሳጭቶ እንደሆነ ተነግሯል

የ60 ዓመት እድሜ ያለው ጉረቤቱን የገደለው እንዲኔዢያዊው ግሰለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል
በኢንዶኔዢያ የ45 ዓመቱ ጎልማሳ “እስካሁን ለምን አላገባህም” እያለ በተደጋጋሚ የሚጠይቀውን ጉረቤቱን መግደሉ አነጋጋሪ ሆኗል።
ግለሰቡ የ60 ዓመት እድሜ ያለው ጉረቤቱን ነው የገደለው የተባለ ሲሆን፤ ምክንያቱ ደግሞ በተደጋጋሚ “ለምን አላገባህም” በሚለው ጥያቁ በመበሳጨቱ እና በመጎዳቱ እንደሆነ አስታውቋለል።
በኢንዶኔዢያ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ የወንጀል ድርቱ የተፈጸመው ባለፍነው ሳምንት ማክሰኞ በሰሜን ሱማትራ በምትገኘው ደቡብ ታፓኑሊ ነው።
“እስካሁን ለምን አላገባህም” የሚል ጥያቄ በማቅረባቸው የተገደሉት ሰው አስጊም አይራንቶ የተባሉ የ60 ዓመት ጡረተኛ አዛውንት መሆናቸውን የኢንዶኔዢያ ፖሊስ አስውቋል።
የፖሊስ አዛዧ ማሪያ እንደተናገሩት፤ ግድያውን የፈጸመው የ45 ዓመቱ ፓርንዱንጋን ሲርጋር ወንጀሉ በፈጸመበት እለት ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ዱላ ይዞ ወደ ቤት በመግባት ነው ጥቃቱን ያደረሰው።
የ60 ዓመቱ አዛውንት አስጊም ራሳቸውን ለማትረፍ መንገድ ላይ ሮጠው ቢወጥም፤ ሲርጋር ተከትሏቸው በመውጥ በመንገድ ላይ ገፍትሮ ከጣላቸው በኋላ በተደጋጋሚ ጭንቅላታቸውን መደብደቡንም ነው ፖሊስ ያስታወቀው።
በስፍራው የነበሩ ሰዎች ሮጠው ደርሰው አስጊም ማስጣል ችለው የነበረ ሲሆን፤ ወደ ሆስፒታል እየወሰዷቸው እያለ መንግድ ላይ ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።
ፖሊስ ግድያው ከተፈጸመ ከአንድ ሰዓት በኋላ ግድያውን የፈጸመውን ፓርንዱንጋን ሲርጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉም ታውቋል።
ተጠርጣሪው ፓርንዱንጋን ሲርጋር ለምን ግድያውን እንደፈጸመ ሲጠየቅም፤ “እስካሁን ለምን አላገባህም” የሚለው ተደጋጋሚ ጥያቄ እንደጎዳው ለፖሊስ ቃሉን ሰጥቷል።