በአባቷ ቀብር ላይ የ``ታገቢኛለሽ ወይ?`` ጥያቄ ያቀረበው ግለሰብ ድጋፍና ተቃውሞ እያስተናገደ ነው
ድርጊቱ የተፈጸመው ደቡብ አፍሪካ ከሞትስዋና፣ ዚምባብዌና ሞዛምቢክ በምትዋሰንበት የሊምፖፖ ግዛት ነው
ታገቢኛለሽ ወይ የተባለችው እንስት ምንም አስተያየት ባለመስጠት በድንጋጤ ስትመለከተው ነበር
ደቡብ አፍሪካዊ አፍቃሪ የፍቅር አጋሩ በአባቷ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ሳለች ያደረገው ድርጊት ዓለምን እያነጋገረ ነው።
የግለሰቡ ፍቅረኛ አባቷ ከዚህ ዓለም በሞት ለይተውባት ሀዘን ላይ ትገኛለች። ታዲያ ይህ አፍቃሪ ፤ ፍቅረኛው በአባቷ ቀብር ላይ ሳለች ቀለበቱን አዘጋጅቶ ``ታገቢኛለሽ ወይ`` ሲል ጠይቋታል።
ታዲያ ይህ ክስተት ነው ደቡብ አፍሪካውያንን እና ሌሎች የዓለም ሀገራትን ዜጎች ያጋገረው፡፡
ምንም እንኳን ቀብር ስነ ስርዓት ሲፈጸም የጋብቻ ጥያቄ ማቅረብ ያልተለመደና አዲስ ቢሆንም ግለሰቡ ግን ይህንን ከማድረግ ወደኋላ አላለም።
ግለሰቡ የፍቅረኛውን እጅ ስቦ ቀለበት ለማድረግ ሲዘጋጅ የቀብር ስነስርዓቱ ታዳሚ የሆነች ግለሰብ ስትቀርጽ ነበር ተብሏል።
ይህ ድርጊትም በቲክቶክ ላይ ተሰራጭቶ ዓለምን እያነጋገረ መሆኑን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል። ድርጊቱ የተፈጸመው ደቡብ አፍሪካ ከሞትስዋና፣ ዚምባብዌ እና ሞዛምቢክ በምትዋሰንበት የሊምፖፖ ግዛት ነው ተብሏል።
አፍቃሪው ሁሉም የቀብር ስነ ስርዓቱ ታዳሚዎች እንዲሰሙት የድምጽ ማጉያ ተቀብሎ ሲያወራ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ድርጊቱ ተቃውሞም ድጋፍም አስተናግዷል።
በአባቷ ሀዘን ላይ የምትገኘውና ታገቢኛለሽ ወይ የተባለችው እንስት ምንም አስተያየት ባለመስጠት በድንጋጤ ስትመለከተው ነበር ተብሏል።
“ታገቢኛለሽ ወይ” ጥያቄ የቀረበላት ግለሰብ ጥያቄውን ትቀበል አትቀበል እስካሁን ግልጽ አልተደረገም። የግለሰቡን ድርጊት ያወገዙ ሰዎች “እንደት ሀዘን ላይ ሳለች ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል” ሲሉ አውግዘውታል።
በሌላ በኩል የግለሰቡን ድርጊት የደገፉ ሰዎች ደግሞ ምንም ችግር እንደሌለው ገልጸዋል።