ልዩልዩ
የአሜሪካ ኮንግረስ አባል በጠራራ ጸሃይ መኪናቸውን መዘረፋቸው እያነጋገረ ነው
መሳሪያ ደግነው ላስራሯቸው ዘራፊዎች የመኪናቸውን ቁልፍ ያስረኩበት ኮንግረስ አባሏ እንዳልተጎዱ ተነግሯል
ሜሪ ጋይ ስካንሎን በታጠቁ ሁለት ዘራፊዎች ነው መኪናቸውን የተዘረፉት ተብሏል
የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ሜሪ ጋይ ስካንሎን በታጠቁ ሁለት ሰዎች መኪናቸውን ተዘረፉ፡፡
መሳሪያ ደግነው ላስራሯቸው ለሁለቱ ዘራፊዎች የመኪናቸውን ቁልፍ ያስረኩበት ስካንሎን እንዳልተጎዱ ተነግሯል፡፡
የኮንግረስ አባሏ ትናንት ረቡዕ ነው በፔንሲልቫኒያ ግዛት ፊላደልፊያ የተዘረፉት፡፡
አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ባካሄደቻቸው የአየር ድብደባዎች ላይ የፈፀመችውን ስህተት የሚያሳይ ሰነድ ወጣ
ሆኖም ዘራፊዎቹ መኪናዋን ይዘው ብዙም ለመሰወር አልቻሉም፡፡ ሲከታተላቸው በነበረው የፈዴራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ.ቢ.አይ) እና በአካባቢው ፖሊስ ተይዘው መኪናዋን ከሰዓታት ቆታ በኋላ መልሰዋል፡፡
የ62 ዓመቷ የዴሞክራትፓርቲ የኮንግረስ ተወካይ በአካባቢው የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቀው ሲወጡ ነው በጠራራ ጸሃይ መኪናቸውን የተዘረፉት፡፡
በትሪሊዮን ከሚቆጠረው የአሜሪካ የኮሮና ማገገሚያ በጀት ውስጥ በትንሹ መቶ ቢሊዮን ዶላር ተሰርቋል ተባለ
ዘራፊዎቹ ከ20 እስከ 30 ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው ያለው ፖሊስ አንድን ሴት ጨምሮ አምስት ተጠርጣሪዎችን መያዙንና መኪናው ለባለቤቱ መመለሱን አስታውቋል፡፡