ሱዳን በተመድ መጋዘኖች ላይ የሚደረጉ ዘርፋዎችን ለማስቆም በዳርፉር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇን አስታውቃለች
የሱዳን መንግስት በሰሜን ዳርፉር ግዛት የሰዓት እላፊ አውጀዋል። በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት (ተመድ) መጋዘኖች እና በአካባቢው ባሉ ሌሎች አለም አቀፍ አካላት ላይ ያነጣጠረውን ሰፊ ዘረፋ ለመቆጣጠር ሰአት እላፊ መታወጁን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የሰሜን ዳርፉር ግዛት የጸጥታ ኮሚቴ በመንግስት ዋና መሥሪያ ቤት በኤል ፋሸር ዋና መሥሪያ ቤት ባደረገው አስቸኳይ የጸጥታ ሁኔታ ላይ በመነጋገር ላልተወሰነ ጊዜ የሰአት እላፊ መጣሉ ተገለጸ።
ማክሰኞ ማምሻውን በኤል ፋሸር በሚገኘው የአለም የምግብ ፕሮግራም (ደብሊውኤፍፒ) መጋዘኖች እንዲሁም በዳርፉር የተባበሩት መንግስታት-የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ዩናመሜድ (UNAMID) ዋና መስሪያ ቤት እና ንብረቶች ላይ ሰፊ ዘረፋ መፈጸሙ ታውቋል።
የሰሜን ዳርፉር ግዛት ፖሊስ አዛዥ አብዱልከሪም ሃምዶ የአካባቢው ነዋሪዎች ለደህንነታቸው ሲሉ የሰዓት እላፊ አዋጁን እንዲያከብሩ አሳስበዋል።
ይህ በንዲህ እንዳለ የአይን እማኞች እንዳሉት በኤል ፋሸር 6 ባለ አራት ጎማ ተሽከርካሪዎች ላይ የታጠቀ ቡድን የደብሊው ኤፍፒ መጋዘኖችን በመውረር የምግብ ቁሳቁሶችን በመዝረፍ መጋዘኖቹን ከሚጠብቀው ሃይል ጋር በመጋጨቱ እስካሁን የደረሰ ጉዳት አልደረሰም ብለዋል።
በኤልፋሸር የሚገኘው የዩናመሜድ(UNAMID)የሎጂስቲክስ መሰረትም በታህሳስ 26 መዘረፉም ተነግሯል።የሱዳኑ ዳርፉር ግዛት በሱዳን አማጺያን የሚንቀሳቀሱበትና ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥስት ተፈጽሞበታል የሚባል ግዛት ነው፡፡