ፖለቲካ
በትግራይ ክልል የመከላከያ ባልደረሰባቸው አካባቢዎች የተደራጁ ዘረፋዎች እየተካሄዱ መሆኑን መንግስት አስታወቀ
ለዝርፊያ የግጭት አትራፊዎች ተጠያቂ እንደሚሆኑ መንግስት አስታውቋል
በተለይም በመቀሌ ከተማ በመንግስትና በንግድ ተቋማት ላይ በፓትሮል የታገዘ ከፍተኛ ዝርፊያ መኖሩን ገልጿል
የኢትዮጵያ መንግስት "የመከላከያ ሰራዊት ባልደረሰባቸው" የትግራይ አካባቢዎች በተለይም በመቀሌ ከተማ የተደራጀ ዝርፊያ እየተፈጸመ ነው ብሏል።
ለዝርፊያው ደረሱኝ ያላቸውን መረጃዎችን የጠቀሰው መንግስት ወንጀል የሚፈጽሙ ሰዎች ከተጠያቂነት አያመልጡም ብሏል።
"የመቀሌ ህዝብ ደህንነት ሊጠበቅ ይገባዋል" ያለው
- የትግራይ ታጣቂዎች ከጦር ግንባሮች ለቀው መውጣት መጀመራቸው ተገለጸ
- መንግስት "የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዕቅድ በተመለከተ ምክክር እየተደረገ ነው” አለ
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፤ የሽግግር ወቅቱን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም የመከላከያ ኃይል ባልደረሰባቸው የትግራይ አካባቢዎች ህብረተሰቡን
ሰላም የሚነሡ የተደራጁ ዘረፋዎች እየተካሄዱ ናቸው ብሏል።
በተለይም በመቀሌ ከተማ በመንግስትና በንግድ ተቋማት ላይ በፓትሮል የታገዘ ከፍተኛ ዝርፊያ መኖሩን ገልጿል።
ህዝቡም በከፍተኛ ምሬት ላይ መሆኑን የጠቀሰው የመንግስት ቃል-አቀባዩ፤ የግጭት አትራፊዎች ይሄንን እንደሚያደርጉ አያጠራጥርም ብሏል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው "የሕዝብ ደህንነት የሚገዳቸው አካላት" ወንጀለኞችን እንዲታገሉ ጥሪ አድርጓል።
የሕዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ ያለብኝን ኃላፊነት ለመፈጸም አስፈላጊውን ሁሉ አደርጋለሁም ብሏል።