ጌታ በህልሜ ነግሮኛል በሚል ሚሊዮን ዶላሮችን ያጭበረበረው ሰባኪ ታሰረ
ሰባኪው ጌታ ምናባዊ ገንዘብ እንድናቋቁም ይፈልጋል በሚል ከተከታዮቹ ከ3 ሚሊዮን በላይ ዶላር ሰብስቧል
በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ይህ ሰባኪ ምን አልባት የጌታን ቃል ስተረጉም አሳስቼው ሊሆን ይችላል ብሏል
ጌታ በህልሜ ነግሮኛል በሚል ሚሊዮን ዶላሮችን ያጭበረበረው ሰባኪ ታሰረ፡፡
በሀገረ አሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት ኤሊ ሪጋላዶ የተሰኘ የሀይማኖት መምህር በሚያገለግልበት ቤተ ክርስቲያን ለሚያዘወትሩ ተከታዮች ጌታ ምናባዊ ገንዘብ ወይም ክሪፕቶ ከረንሲ እንድናቋቁም በሕልሜ ነግሮኛል በሚል ይነግራቸዋል፡፡
የሰባኪያቸውን ሕልም ያመኑት እነዚህ አማኞችም በየጊዜው ገንዘባቸውን በዚህ ሰባኪ ስር ለተቋቋመው ኢንዴክስ ኮይን ለተሰኘው ድርጅት ያስገባሉ፡፡
ይህ በጌታ ፈቃድ ተቋቋመ ለተባለው የምናባዊ ገንዘብ ትርፉ እያደገ እንደሆነ ዘላለማዊ የኝግድ ተቋም እንደተመሰረተ በየጊዜው ይነግራቸው እንደነበር ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም የአሜሪካ የደህንነት ተቋም ሰራተኞች ጉዳዩን መመርመር ሲጀምር ሰባኪው 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የተጭበረበረ ገንዘብ እንዳለ ይረዳሉ፡፡
የሩሲያው ምናባዊ ገንዘብ ተቋም በኢትዮጵያ የዳታ ማዕከል ሊከፍት መሆኑን አስታወቀ
ፖሊስም ሰባኪ ኤሊ ሪጋላዶን እና ካቲልን የተሰኘች ሚስቱን በቁጥጥር ስር አድርጎ ባደረገው ማጣራት መምህሩ ከቤተ ክርስቲያኗ ተከታዮች እንደሰበሰበው ይደረስበታል፡፡
ለሰባኪው ለምን ከተከታዮችህ አጭበርብረህ ገንዘብ ተቀበልክ? በሚል ለቀረበለት ጥያቄ ምን አልባት የጌታን መልዕክት በህልም መልክ ስረዳ አሳስቼ ተርጉሜው ሊሆን ይችላል ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ይህ ሰባኪ ከቤተ ክርስቲያኗ ተከታዮች ከሰበሰበው አጠቃላይ ገንዘብ ውስጥ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ያህሉን ለግል ፍላጎቱ እንዳጠፋው ተገልጿል፡፡
እንዲሁም በባለቤቱ እና በእሱ ስም ቅንጡ ተሽከርካሪዎች፣ ጌጣጌቶች እና ሌሎች መገልገያዎችን ገዝቷልም ተብሏል፡፡