አሜሪካ በዩክሬን ጉዳይ የአቋም ለውጥ ማድረጓ ተገለጸ
ዩክሬን በሩሲያ የተወሰዱባትን ግዛቶች ከማስመለስ ይልቅ ያላትን ይዛ እንድትቆይ ማድረግ ላይ ማተኮሯ ተገልጿል
ሩሲያ ተጨማሪ የዩክሬን ግዛቶችን እንዳትወስድ ማድረግ የአሜሪካ አዲሱ ስልት ነው ተብሏል
አሜሪካ በዩክሬን ጉዳይ የአቋም ለውጥ ማድረጓ ተገለጸ፡፡
ለሁለት ሳምንት በሚል የተጀመረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ሁለት ዓመት ሊሞላው ቀናት ብቻ ይቀሩታል፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በርካታ ክስተቶች የተፈጠሩ ሲሆን ጉዳቱ ከዩክሬን እና ሩሲያ አልፎ በመላው ዓለም ላይ የምግብ እና ነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር አድርጓል፡፡
ሩሲያ አራት ግዛቶችን ከዩክሬን ወደ ራሷ በህዝበ ውሳኔ የጠቀለለች ሲሆን ዩክሬን በመልሶ ማጥቃት ዘመቻ የተወሰኑ ቦታዎችን ማስመለስ ችላለች፡፡
ይሁንና ሩሲያ ዳግም ተጨማሪ ግዛቶችን ከዩክሬን በመውሰድ ላይ መሆኗን ተከትሎ አሜሪካ ለዩክሬን በምታደርገው ድጋፍ ዙሪያ የአቋም ለውጥ ማድረጓ ተገልጿል፡፡
እንደ ዋሸንግተን ፖስት ዘገባ ከሆነ አሜሪካ ዩክሬን ተጨማሪ ግዛቶች በሩሲያ እንዳይወሰድባት ድጋፍ ወደ ማድረግ ተለውጧል ብሏል፡፡
የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳድር ለዩክሬን ተጨማሪ ድጋፍ ማድረግ እንዳይችሉ በኮንግረሱ ተቃውሞ መግጠሙን ተከትሎ አዲስ የድጋፍ እቅድ እንዲያወጡ አድርጓቸዋል ተብሏል፡፡
በዚህም መሰረት ሩሲያ ተጨማሪ የዩክሬን ግዛቶችን መያዝ እንዳትችል እና የኢኮኖሚ ጉዳት እንዲደርስባት የሚያደርግ ሲሆን በረጅም ጊዜ ደግሞ ወደ ሩሲያ የተጠቃለሉ ግዛቶችን ማስመለስ መታሰቡም ተገልጿል፡፡
በዮርዳኖስ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 3 የአሜሪካ ወታደሮች ሲገደሉ ከ34 በላይ ቆሰሉ
አዲሱ የአሜሪካ እቅድ ወደ ስልጣን እንደሚመጡ የሚጠበቁት ዶናልድ ትራምፕ እንደማይቃወሙት ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ለዩክሬን እያደረገችው ያለው ድጋፍ የተጋነነ እና የአሜሪካንን ኢኮኖሚ የሚጎዳ ነው በሚል መቃወማቸው ይታወሳል፡፡
የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶ ዋና ጸሃፊ ጀንስ ስቶልንተበርግ በበኩላቸው የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ዓመታዊ በጀት ለዩክሬን ድጋፍ ሊውል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡