በፓሪስ በኢራን ቆንስላ ደጃፍ ራሱን ለማቃጠል ሲያስፈራራ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
ክስተቱ በአሁነ ወቅት በእስራኤል እና ኢራን መካከል ካለው ውጥረት ጋር ስለመያያዙ የታወቀ ነገር አለመኖሩ ተገልጿል
ግለሰቡ ቦምብ እና ተቀጣጣይ የሚመስል ቁስ ይዞ ዛሬ ረፋድ ወደ ቆንስላው ውስጥ ገብቶ ነበር
በፓሪስ በኢራን ቆንስላ ደጃፍ ራሱን ለማቃጠል ሲያስፈራራ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።
የፈረንሳይ ፖሊስ ፓሪስ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ደጃፍ ራሱን ለማቃጠል ሲያስፈራራ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አዋለ።
ሮይተርስ የፖሊስ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ግለሰቡ ቦምብ እና ተቀጣጣይ የሚመስል ቁስ ይዞ ዛሬ ረፋድ ወደ ቆንስላው ውስጥ ገብቶ ነበር። ፖሊስም አካባቢውን አጥሮት ቆይቶ ነበር።
ግለሰቡ ቆይቶ ከቆንስላው መውጣቱን እና ምንም ተቀጣጣይ ነገር አለመያዙን የፖሊስ ምንጮች መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ሊ ፓሪሲየን የተባለው ጋዜጣ በጽረ ገጹ ላይ ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ግለሰቡ በቆንስላው ደጃፍ ላይ ሰንደቅ አላማ አንጥሮ የወንድሙን ሞት መበቀል እንደሚፈልግ ተናግሯል።
ክስተቱ በአሁነ ወቅት በእስራኤል እና ኢራን መካከል ካለው ውጥረት ጋር ስለመያያዙ የታወቀ ነገር አለመኖሩ ተገልጿል።
በዛሬው እለት ጠዋት እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ማድረሷ ተዘግቧል፤ ነገርግን የኢራን ባለስልጣናት እና መገናኛ ብዙኻን ጥቃቱን በሰርጎገቦች የተፈጸመ ነው ሲሉ አቃለውታል።
በጥቃቱ የደረሰው ጉዳት ዝቅተኛ መሆኑን የገለጸችው ኢራን ለዚህ ጥቃት እስራኤልን አልወነጀለችም፤ የበለቀል እርምጃ የመውሰድ እቅም እቅድ እንደሌላትም አመላክታለች።