ብልቱን ለማርዘም አምስት ሺህ ዩሮ የከፈለው ሰው በመጨረሻም ሐኪሙን ለመክሰስ ተገዷል
የ40 ዓመቱ ጣሊያናዊ 12 ዙር የፈጀ ቀዶ ጥገና ህክምና ቢያደርግም የጠበቀው እንዳልሆነ ይናገራል
ጉዳዩን የተመለከተ ፍርድ ቤትም ቀዶ ጥገናውን ያደረገው ሐኪም እና ተቋሙ 165 ሺህ ዶላር ካሳ እንዲከፍሉ ወስኖባቸዋል
ብልቱን ለማርዘም ከአምስት ሺህ ዩሮ የከፈለው ሰው በመጨረሻም ሐኪሙን ለመክሰስ ተገዷል፡፡
የ40 ዓመቱ ጣልያናዊ በቱስካኔ የሚኖር ሲሆን ከአንድ ወር በፊት ነበር ወደ አንድ የቀዶ ጥገና ሕክምና ተቋም ጎራ ያለው፡፡
ይህን ሰው ወደ ህክምና ተቋም የወሰደው ጉዳይ የብልቱን መጠን ለማርዘም ነበር የተባለ ሲሆን 12 ዙር የፈጀ ቀዶ ጥገና ሕክምና ማድረጉ ተገልጿል፡፡
ታካሚውም ለዚህ ህክምና ሲባል ከፍተኛ ወጪ ባወጣም የጠበቅኩት አልሆነም በሚል በድጋሚ ወደ ህክምና ተቋሙ ይመለለሳል፡፡
ከሐኪሞቹ ጋር መስማማት ያልቻለው ይህ ሰው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶ ክስ ሊመሰርት እንደቻለ የጣልያኑ ረፕብሊካ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ክስ የተመሰረተበት የቀዶ ጥገና ሐኪም ህክምናውን ያደረኩት ፈቃደኝነቱን ጠይቄ ነው፤ ከህክምናው በኋላ ደስተኛ ደስተኛ መሆኑን የሚያሳይ የቪዲዮ ማስረጃም አለኝ ሲል ተከራክሮ ነበር፡፡
የጣፊያ ህክምና ለማግኘት ወደ ሆስፒታል የገባው ታካሚ በስህተት የወንድ የዘር ፍሬ ቱቦውን አጣ
ፍርድ ቤቱም በጉዳዩ ላይ የባለሙያዎችን አስተያየት በግብዓትነት በመውሰድ የቀዶ ህክምናውን ያደረገው ሐኪም እና የህክምና ተቋም ስህተት መስራታቸውን፣ ታካሚዎች ህክምናው ሊጎዳቸው እንደሚችል ላያውቁ ስለሚችሉ ማስተማር መቅደም የነበረበት ቢሆንም ይህንን ሐላፊነታቸውን አልተወጡም ሲል የጥፋተኛ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
እንዲሁም ጣልያን በህክምና አገልግሎት ወቅት ጥቅም ላይ እንዳይውል እገዳ የጣለችበትን አካል ሐኪሙ እና የሕክምና ተቋሙ ተጠቅመው ተገኝተዋል፤ ታካሚው ለከፋ ጉዳት እንዲዳረግ ምክንያት ሆናችኋል በሚል ለተጎጂው 153 ሺህ ዩሮ ካሳ እንዲከፍሉ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ይሁንና ህክምና ፈልጎ የሄደው ግለሰብም የተወሰኑ ጥፋቶችን ሰርቷል በሚል የገንዘብ ቅጣቱን ከ153 ሺህ ዩሮ ወደ 110 ሺህ ዩሮ ዝቅ ሲያደርግ ከዚህ ውስጥ 70 በመቶውን የቀዶ ጥገና ህክምናውን ያደረገው ሐኪም ይክፈል ሲል መወሰኑ ተገልጿል፡፡