መስል ክስተት ከ500 ሺህ ህጻናት በአንዱ እንደሚከሰት ባለሙያዎች ይናገራሉ
በህንድ ናግፑር ከተማ ነዋሪ የሆነው ሳንጁ ባጋት ለ36 አመት የዘጠኝ ወር ነፍሰጡር መስሎ ለመቆየት ተገዷል።
ከተወለደ አንስቶ የሆዱ መጠን እያደገ የመሄዱና ምንም አይነት የመጉደል ምልክት አላሳይ ማለቱን ተከትሎም በማህበረሰቡ የተለያየ ስያሜ ሲሰጠው ቆይቷል።
“ወንዱ ነፍሰጡር” የሚል ቅጽል ስም ወጥቶለት ማሸማቀቁ ቢበዛበትም ቤተሰቦቹን ማገዝን የመረጠው ባጋት በ36 አመቱ ግን የማይችለው ፈተና ይገጥመዋል።
ለሶስት አስርት አመታት ችሎት የቆየው የሆዱ እብጠትና ህመም ከቁጥጥሩ ውጭ ሲሆን በፈረንጆቹ 1999 ወደ ሙምባይ ሆስፒታል በአምቡላንስ ያመራል።
የወቅቱን ክስተት የሚያስታውሱት ዶክተር አጃይ ሜህታ፥ ባጋታን ነፍሰጡር ያስመሰለው የሆድ እብጠት በቀዶ ህክምና ለማስወገድ አስቸግሮ እንደነበር ይናገራሉ።
“ቀዶ ህክምናውን እንደጀመርን ያልጠበቅነው ነገር ገጠመን፤ እጄ ይንቀጠቀጥ ነበር፤ ከባጋት ሆድ ውስጥ አጥንት እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ወጥተዋል” ይላሉ ዶክተር አጃይ።
ክስተቱ ድንጋጤም አግራሞትም መፍጠሩን የሚናገሩት ዶክተር አጃይ፥ ከባጋት ሆድ የወጣው የመንትያው የሰውነት ክፍሎች ናቸው ይላሉ።
ያልተሟላውና ፍጡር እጅና እግር ያለው ሲሆን ጥፍሮቹም ረጃጅም ናቸው።
እንዲህ አይነት ክስተት በ500 ሺህ ጽንስ በአንዱ እንደሚከሰት ጥናቶች የሚያመላክቱ ሲሆን አሁንም ድረስ በርካቶችን ማስገረሙን ቀጥሏል።
ለ36 አመት ሲሰቃይ የቆየው ህንዳዊ አሁን በቀዶ ህክምና “ተገላግሎ” ጤናማ ህይወት እያሳለፈ እንደሚገኝ ኤቢሲ ኒውስ ዘግቧል።