የቀድሞው የሊቨርፑል አማካኝ ተጫዋች ጄራርድ የአስቶን ቪላ እግር ኳስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሾሟል
የቀድሞው የሊቨርፑል አማካኝ ስቴቨን ጄራርድ የአስቶን ቪላ አሰልጣኝ ሆነ፡፡
የ41 ዓመቱ ጄራርድ ለቀጣዩ ሶስት ዓመት ከመንፈቅ አስቶን ቪላን በዋና አሰልጣኝነት ይመራል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ከ20 በታች የሴቶች የሴካፋ ውድድር ዋንጫ አሸነፈች
የቀድሞው የሊቨርፑል አማካኝ እና አምበል ስቴቨን ጄራርድ የአስቶን ቪላ አሰልጣኝ ሆኖ ከመሾሙ በፊት በስኮትላንድ ሊግ የሚወዳደረውን ሬንጀርስን ያሰለጥን ነበር፡፡
ጣልያናዊው አንቶኒዮ ኮንቴ የቶትንሀም አሰልጣኝ ሆነው ተሸሙ
አስቶን ቪላ ከአንድ ሳምንት በፊት የክለቡን አሰልጣኝ ዲን ስሚዝን በውጤት ማጣት ምክንያት ካሰናበተ በኋላ ጄራርድን መቅጠሩን አስታውቋል፡፡
አስቶን ቪላ ስቴቨን ጄራርድን ከሬንጀርስ ለማምጣት 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዩሮ ካሳ መክፈሉን መግለጹንም ነው ስካይ ስፖርት የዘገበው፡፡
ዲዲዬር ድሮግባ የዓለም ጤና ድርጅት አምባሳደር ሆነ
ጄራርድ ለሊቨርፑል 710 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን 9 ዋናጫዎችን ከክለቡ ጋር አሸንፏል፡፡
በስቴቨን ጄራርድ አሰልጣኝነት የመጀመሪያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን ከብራይተን ጋር የሚያደርገው አስቶን ቪላ በቀጣይ ከማንችስተር ሲቲ፣ ከሊቨርፑል እና ከቸልሲ ጋር ከባድ ጨዋታዎችን ያደርጋል፡፡