የኔልሰን ማንዴላ ታዋቂ ሸሚዝና ሌሎች ንብረቶች ለሽያጭ ቀረቡ
ማንዴላ በፈረንጆቹ2013 በ95 አመታቸው በጆሃንስበርግ ነበር ህይወታቸው ያለፈው
ሰዎች የማስታወሻ ፓርኩን ጎብኝተው ሲጨርሱ፣ከማንዴላ ምን ትምህርት መውስድ አለብኝ ብለው እንዲያስቡ ያደረጋል ብለዋል የማንዴላ ልጅ ዶክተር ማካዚዌ ማንዴላ
የሟቹ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ ቤተሰቦች፣ ለማንዴላ ማስታወሻ ፓርክ ግንባት የሚሆን ገቢ ለማግኘት የማንዴላን ንብረቶች ለሽያጭ አቅርበዋል፡፡
ለሽያጭ ከቀረቡት 100 ቁሳቁስዎች መካከል፤ ማንዴላ በፈረንጆቹ 1998 እና በ2003 በነበሩ መደበኛ ዝግጅቶች ላይ የእንግሊዟን ንግስት ኤልሳቤትን ሲያገኙ ጭምሮ የለበሷት ተወዳጇ የማዲባ ሸሚዝ ትገኛለች፡፡
መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው ጎርንሰይ የተባለው የጨረታ አውጭ ድርጅት ሸሚዟ ማንዴላን ከሌሎች መሪዎች ትለየው ነበር ብሏል፡፡ ድርጅቱ ጨረታውን በፈረንጆቹ ታህሳስ 11 በኦንላይ እንደሚያቀርብ መግለጹን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ኔልሰን ማንዴላ የተቀበሩበትንና በቁኑ የሚገኘውን የኔልሰን ማንዴላን ማስታወሻ ፓርክ ለመገንባት ከባራክ ኦባማና ከሌሎች ሀገራት መሪዎች የተበረከተላቸውን እና የማንዴላን መነጽር፣ ዋሌት፣ፓንትና ሌሎችም ቁሳቁሶች ለሽያጭ ቀርበዋል፡፡
ማንዴላ በፈረንጆቹ 2013 በ95 አመታቸው በጆሃንስበርግ ነበር ህይወታቸው ያለፈው፡፡ የማንዴላን ቤተሰባዊ ህይወት የሚያሳዩ ቁሳቁሶች በማንዴላ ማስታወሻ ፓርክ ይቀመጣሉ ተብሏል፡፡
ዶክተር ማካዚዌ ማንዴላ እንደታገረው ኔልሰን ማንዴላ በተወለዱበት ምስራቃዊ ጫፍ ቱሪዝም ማስፋፋት ይፈልግ ነበር፤ስለሆነም ይህ እውን እንዲሆን የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡
ሰዎች የማስታወሻ ፓርኩን ጎብኝተው ሲጨርሱ፣ከማንዴላ ምን ትምህርት መውስድ አለብኝ ብለው እንዲያስቡ ያደረጋል ብለዋል ዶክተር ማካዚዌ ማንዴላ፡፡ የፓርኩ የመጀመሪያው ግንባታ ሂደት መጠናቀቁን ዶክተር ማካዚዌ ማንዴላ ገልጸዋል፡፡
የማንዴላ 10ሸሚዞች በኒውዮርክ የፋሽን ኢንስቲትዮት ኦፍ ቴክኖሎጂ ያሉ ተማሪዎችንና ሌሎች ማህበረሰቦችን ለማስተማር ለሶስት ሳምንታት ለሽያጭ መቅረባቸውን የሙዚየሙ ምክትል ዳይሬክተር ፓትሪሻ ሚርስ ተናግረዋል፡፡