ደቡብ አፍሪካዊው የጸረ-አፓርታይድ ታጋይ በ95 አመታቸው ሞቱ
ፕሬዘዳንት ሲርል ራማሮዛ፣ ምላንገኒን ለፍትሃዊ አመራርና ለሰው ልጅ ጠበቃ ነበሩ ሲሉ ገልጸዋቸዋል
ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ታስረው የነበሩት የጸረ-አፓርታይድ ታጋይ አንድሬው ምላንገኒ በ95 አመታቸው ሞቱ
ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ታስረው የነበሩት የጸረ-አፓርታይድ ታጋይ አንድሬው ምላንገኒ በ95 አመታቸው ሞቱ
በሀገር ክህደት ክስ ከኔልስን ማንዴላ ጋር በፈረንጆቹ 1964 ታስረው የነበሩት ደቡብ አፍሪካዊ የጸረ-አፓርታይድ ታጋይ አንድሬው ምላንገኒ በ95 አመታቸው ህይወታቸው አልፏል፡፡
ለ26 አመታት የታሰሩት ከሞቱት የመጨረሻዎቹ ስምንት ተከሳሾች መካከል ሲሆኑ በጨጓራ በሽታ ምክንያት ሆስፒታል ገብተው እንደነበረ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከምላንገኒ ጋር ለዘር እኩልነትና የነጭ የበላይነት ለማስቆም የታገሉት የአሁኑ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ሲርል ራማሮዛ፣ ምላንገኒን የፍትሃዊ አመራርናየሰው ልጅ ጠበቃ ነበሩ ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡ ፕሬዘዳንቱ እንዳሉት የምላንገኒ ሞት የአንድ ትውልድ ታሪክ የሚያበቃበትና የወደፊቱን ሁኔታ አሁን በቀረው ላይ የተው ነው ብለውታል፡፡
“ምላንገኒ በሞታቸው…ለነጻነቷ የተዋደቁላትን ደቡብ አፍሪካን እንዲገነቡ ዱላውን ለሀገራቸው ልጆች አሳልፈው ሰጥተዋል ”ብለዋል ፕሬዘዳንት ራማፎዛ፡፡
ፕሬዘዳንቱ ከዚህ በተጨማሪም የምላንገኒ ህይወት ለጀግንነትና ሰብአዊነት ምሳሌ ነበር ብለዋል፡፡
ምላንገኒ በፈረንጆቹ 1925 ነበር የተወለዱት፡፡ በፈረንጆቹ 1951፣ ምላንገኒ አሁን ስልጣን ላይ ያለው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ የወጣቶች ክንፍ በመሆን የተቀላቀሉ ሲሆን ቆይተውም ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ውጭ ተልከው ነበር፡፡