ነጩ የደቡብ አፍሪካ የፀረ-አፓርታይድ ታጋይ በ87አመታቸው ሞቱ
ነጩ የደቡብ አፍሪካ የፀረ-አፓርታይድ ታጋይ በ87አመታቸው ሞቱ
ደቡብ አፍሪካዊው የፀረ-አፓርታይድ አክቲቪስት ዴኒስ ጎልድበርግ በ87 አመታቸው በቤታቸው ህይወታቸው አለፈ፡፡
ጎልድበርግ አሁን ሀገሪቱን እየመራ ያለው የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ አባል የነበሩና ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ታስረው የነበሩ ናቸው፡፡
ጎልድበርግ በነጭ አናሳ ቡድን የተጣለውን አፓርታይድ ሲስተም በመታገላቸውና በአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ በነበራቸው ተሳትፎ ለ22 ዓመታት ያህል ታስረዋል፡፡
የጎልድበርግ ጓዶች ወደ ሮቢን ደሴት ሲላኩ፣ ነጩ እስረኛ ከነሱ ተነጥሎ በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ፕሪቶሪያ ተነጥሎ እንዲታሰር ሆኗል፡፡
የጎልድ በርግ የወንድም ልጅ እንደገለጹት የነፃነት ታጋዩ በሳንባ ካንሰርና በስኳር በሽታ ከታመሙ በኋላ በትናንትናው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡
ጎልድበርግ አፓርታይድ ከተሸነፈ በኋላም በአክቲቪስትነት ቀጥለው በፈረንጆቹ በ2018 ከስልጣን የወረዱትን የቀድሞውን ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ይተቹ ነበር፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ጎልድበርግ የበአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ የደሀ ጥቁሮችን ህይወት ለመቀየር ያደረገውን እንቅስቀሴ ይተቹ ነበር፡፡ ጎልድበርግ በፀረ-አፓርታይድ ትግል ባበረከቱት እንቅስቀሴ ብዙዎች እያሰቧቸው ነው፡፡
ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎዛ ጎልድበርግን ስነምግባር ለተላበሰው አመራሩና በጎልማሳነት እድሜያቸው የቀድሞ ታጋዮችን እንቅስቃሴ በመመስረት ቁርጠኝነት አሳይተዋል ብለዋል፡፡
ራማፎዛ ጎልድቤርግ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሁሌም በፀሎታችን እናስባቸዋልን ብለዋል፡፡