የደቡብ አፍሪካ ፍ/ቤት የአካባቢያዊ ምርጫ እንዲራዘም የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገ
ገዥው ፓርቲአፍሪካ ብሄራዊ ኮነግረስ የፍ/ቤቱን ውሳኔ አይደግፈውም ተብሏል
ፍርድቤቱ ምርጫ ከፈረንጆቹ ጥቅምት 27 እስከ ህዳር ድረስ ባለው ጊዜ መደረግ አለበት የሚል ውሳኔ አስተላልፏል
የደቡብ አፍሪካ ፍርድቤት የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን በፈረንጆቸቹ ጥር 27 ሊደረግ የነበረው የአካባቢያዊ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገው፡፡
ውሳኔው የምርጫው መራዘም ለሚደግፈው ለገዥው ፓርቲ (ለአፍሪካ ብሄራዊ ኮነግረስ) ኪሳራ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በፈረንጆቹ 2016 በተካሄደው ምርጫ ገዥው ፓርቲ ጆሃንስበርግን የመሰሉ ቁልፍ ከተሞችን ተቀናቃኝ ለሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስረክቧል፤ ውጤቱ በሀገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ መካሄድ ከጀመረ ወዲህ ትልቅ ኪሳራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ ምርጫ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝና በሙስና የተጠረጠሩትን የቀድሞውን ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማን መታሰር ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት በኋላ የሚደረግ በመሆኑ ለገዥው ፓርቲ መፈተኛ ይሆናል ተብሏል፡፡
የገዥው ፓርቲ ቃል አቀባይ ለሀገሪቱ ቴሌቪዥን ኤስኤቢሲ እንደተናገሩት የፍድቤቱን ውሳኔ እንደሚቀበሉና አስተያየት ለመስጠት ግን ውስኔ በጥልቀት እንደሚያዩት አስረድተዋል፡፡
የምርጫ ኮሚሽኑ ምርጫው እንዲራዘም ወደ ፍርድቤት አለመልክቶ የነበረው በነሀሴ ወር ነበር፡፡ ፍርድቤቱ ባሳለፈው ውሳኔ፤የመንግስትን ውሳኔ ወደ ጎን በመተው ምርጫው ከፈረንጆቹ ጥቅምት 27 እስከ ህዳር ድረስ ባለው ጊዜ መደረግ አለበት የሚል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡